በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

“ለመጭው አደገኛ የሙቀት ማዕበል ሙቀት፣ የተሻለ ዝግጅት ያስፈልጋል” ተመድ እና ቀይ መስቀል


በአየር ንብረት ለውጥ እና በድርቅ ምክንያት አካባቢያቸውን ለቀው የተሰደዱ ሶማሊያውያን፣ በዶላ፣ ሶማሊያ 09/20/22
በአየር ንብረት ለውጥ እና በድርቅ ምክንያት አካባቢያቸውን ለቀው የተሰደዱ ሶማሊያውያን፣ በዶላ፣ ሶማሊያ 09/20/22

የዓለም ቀይ መስቀል እና የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በቅርቡ በካሊፎርኒያ ሳክራሜንቶ እንዲሁም ሶማሊያ እና ሽችኋን ቻይናን ያዳረሰውን የመሰለ ብዙ ህይወት ሊቀጥፍ የሚችል አደገኛ ሙቀት ለመከላከል የተሻለ ዝግጅት ማድረግ እንደሚገባ አሳሰቡ፡፡

በመንግሥታት እና በህዝብ ብዙ መሰራት እንዳለበት ያሳሰቡት የተባበሩት መንግሥታት የሰብዓዊ ጉዳዮች ቢሮ (ኦቻ) የዓለም አቀፍ ቀይ መስቀል ፌደሬሽን እና የቀይ ጨረቃ ማኅበራት ከትናንት በስቲያ ባወጡት የመጀመሪያው የጋራ ሪፖርታቸው ነው፡፡

ድርጅቶቹ በሪፖርታቸው በአደገኛ የግለት ማዕበሎች እስከዛሬ የደረሱ ውድመቶች የዘረዘሩ ሲሆን ወደፊት የሚያስከትለውን ጥፋት ለመቀነስም ከወዲሁ መዘጋጀት የሚቻልበትን መንገድ አመላክተዋል፡፡

“ለወደፊቱ ከባድ ሙቀት መዘጋጀት” ‘Extreme Heat: Preparing for the Heatwaves of the Future,’ በሚል ርዕስ የወጣው ሪፖርት፣ እአአ ከ2010 እስከ 2019 ድረስ በዓለም ከ70ሺ በላይ ለሚሆኑ ሰዎች ሞት ምክንያት የሆኑ 38 ከባድ የሙቀት ወቅቶች መከሰታቸውን አመልክቷል፡፡

XS
SM
MD
LG