ዋሺንግተን ዲሲ —
ባለፈው ወር አፍጋኒስታን ውስጥ ከተካሄደው የምክር ቤት ምርጫ ጋር በተያያዘ በተቀሰቀሰው አመጽ፣ ከ400 በላይ የአፍጋን ሕዝብ መሞቱን ተመድ አስታወቀ።
በአፍጋኒስታን የድርጅቱ ልዩ ሚሽን ዛሬ ይፋ ባደረገው መግለጫ መሠረት፣ ባለፈው ጥቅምት 10 ቀን በተካሄደው የመጀመሪያ ቀን ምርጫና በቀጣዮቹ ቀናት ዘግይተው በነበሩ የድምፅ አሰጣጥ ወቅት፤ 56 ሰዎች ሲሞቱ 379 ቆስለዋል።
የድርጅቱ የአፍጋኒስታን ሚሽን እንዳስታወቀው፣ ካለፉት አራት የምርጫ ወቅቶች ይልቅ በአሁኑ ምርጫ በተቀሰቀሰው አመፅ፣ የበለጠ ሕዝብ፣ ሕይወቱን አጥቷል።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ