ዋሺንግተን ዲሲ —
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ትላንት ያወጣው ዘገባ ካለፈው ጥር ወር አንስቶ እስከ መጋቢት በነበሩት ሶስት ወራት ውስጥ የበዙ የአፍጋኒስታን ሲቪሎች የተገደሉት በታሊባንና ሌሎች አማጽያን ሳይሆን በዩናይትድ ስቴትስና በሀገሪቱ መንግሥት ኃይሎች ነው ይላል።
ኻሊሊዛድ በበኩላቸው የሰዎች ሞት “ሁላችንም ያስቆጣል። ግድያውን ከሚቃወሙት አፍጋኖች ጋር ነን። ደም መፋሰሱ እንዲቆም እንፈልጋለን” ሲሉ ዛሬ በትዊተር ገልፀዋል።
በሦስቱ ወራት ውስጥ መንግሥትን በሚደግፉ ኃይሎች የተገደሉት ሲቪሎች 305 ሲሆኑ 303 ቆሰለዋል። በአማጽያን የተገደሉት ሲቪሎች 227 ሲሆኑ የቆሰሉት 736 ናቸው።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ