በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ተመድ ስለ ሮሒንግያ ሙስሊምች ስደተኞች


በማያንማር ምዕራባዊ ራክሄን ግዛት ያለው አመጽ፣ የሮሒንግያ ሙስሊሞችን ከክልሉ ለማስወጣት ሆነ ተብሎ በመንግሥት ኃይሎች ተቀነባብሮ እንደሚካሄድ፣ ተመድ አስታወቀ።

በማያንማር ምዕራባዊ ራክሄን ግዛት ያለው አመጽ፣ የሮሒንግያ ሙስሊሞችን ከክልሉ ለማስወጣት ሆነ ተብሎ በመንግሥት ኃይሎች ተቀነባብሮ እንደሚካሄድ፣ ተመድ አስታወቀ።

የማያንማር ወታደሮች፣ በታጣቂ ቡዲሂስት “ወሮበሎች” በመታገዝ፣ የሮሒንግያ መኖሪያ ቤቶችንና መንደሮችን በማጥፋት ብቻ ሳይወሰኑ፣ በዚያ አካባቢ እንዳልነበሩ የሚያደርግና ደብዛቸውን የሚያጠፋ፣ ጨርሶም እንዳይታወሱ ለማድረግ የሚካሄድ አመፅና እርምጃ ነው ሲል፣ ዛሬ ረቡዕ ጄኔቫ ላይ ይፋ የሆነ የድርጅቱ የሰብዓዊ መብቶች ቢሮ መግለጫ አመልክቷል።

እአአ ካለፈው ነሐሴ ሃያ አምስት ቀን ወዲህ ብቻ፣ ከግማሽ ሚሊዮን በላይ ስደተኞች ናቸው ከማያንማር ወደ ባንግላዴሽ የተሰደዱት።

ከየሮሒንግያ ስደተኞች ጋር በተካሄደውና በ65 ተከታታይ ቃለ መጠይቆች ላይ የተመሰረው የተመድ ዘገባ ግን፣ ራክሄን ውስጥ የማጽዳት ዘመቻ የተባለው እርምጃ የተጀመረው ከወር በኋላ መሆኑም ታውቋል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG