በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የተመድ ዋና ጸኃፊ በእርዳታዎቹ ትግራይና አፋር መድረስ ተደስቻለሁ አሉ


ፎቶ ፋይል፦ ስቴፋን ዱያሪች
ፎቶ ፋይል፦ ስቴፋን ዱያሪች

የተባበሩት መንግሥታት ዋና ጸኃፊ አንቶኒዮ ጎተሬዥ የሰብአዊ እርዳታ በሮችን ክፍት ለማድረግ መወሰኑን ተከትሎ የእርዳታ ምግብና ነዳጅ የጫኑ ተሽካርካሪዎች ትግራይ እና አፋር የመድረሳቸው ዜና ያስደሰታቸው መሆኑን ቃል አቀባያቸው ስቴፋን ዱያሪች ዛሬ በሰጡት መግለጫ አስታወቁ፡፡

ዋና ጸኃፊ ሁሉም ወገኖች እርዳታውን ለሚፈልጉ ሰዎች ተደራሽነትን ለማመቻቸት የገቡትን ቃል በማክበር የጀመሩትን ጥረት እንዲገፉበት አሳስበዋል፡፡

በትግራይ የባንክ፣ የመብራትና የቴሌኮሙኒኬሽን አገልግሎቶችን ጨምሮ የንግድ አገልግሎት ተደራሽነት ወደ ነበሩበት እንዲመለሱም በድጋሚ ጥሪ ማድረጋቸውን ቃል አቀባዩ ገልጸዋል፡፡

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የወደፊቷን ሰላማዊና የበለፀገች ኢትዮጵያን ለመርዳት ከዚህ በፊት የገባውን ጽኑ አቋም በድጋሚ እንደሚያረጋግጥ አመልክቷል።

XS
SM
MD
LG