በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ተመድ በሦርያ በተከበበችው ምሥራቅ ጎታና በደማስቆ የቦንብ ድብደባ እንዲቆም ጥሪ አቀረበ


በሦሪያ በተከበበችው ምሥራቅ ጎታ ላይ የሚዘንበው እጅግ ሰቅጣጭ የቦንብ ድብደባና በደማስቆ ከተማ ላይ የሚወነጨፈው የከባድ መሣሪያ ውርጅብኝ በአስችኳይ እንዲቆም፣ የዓለሙ ድርጅት ልዩ መልዕክተኛ ስታፋን ዲ ሚስቱራ ዛሬ ጥሪ አቅርበዋል።

በሦሪያበተከበበችው ምሥራቅ ጎታ ላይ የሚዘንበው እጅግ ሰቅጣጭ የቦንብ ድብደባና በደማስቆ ከተማ ላይ የሚወነጨፈው የከባድ መሣሪያ ውርጅብኝ በአስችኳይ እንዲቆም፣ የዓለሙ ድርጅት ልዩ መልዕክተኛ ስታፋን ዲ ሚስቱራ ዛሬ ጥሪ አቅርበዋል።

በተባበሩት መንግሥታት ቃል አቀባይ ጄኔቭ ላይ የተነበበው የዲ ሚስቱራ የተኩስ አቁም ጥሪ ሦስቱ የአስተራው የሰላም ሂደት ፈራሚዎች ሩሲያ ኢራንና ቱርክ በአስችኳይ ተሰብስበው በሦሪያ ውጊያው እንዳይባባስ መፍትሄ መሻት አለባቸው ይላል።

ይህ የስታፋን ዲ ሚስቱራ አስተያየ የተሰጠው የተባበሩት መንግሥታት የፀጥታው ምክር ቤት በሦሪይ ለ30 ቀናት የተኩስ አቁም እንዲደረግ በሚሰጥ ውሳኔ ላይ ድምፅ ከመስጠቱ ጥቂት ሰዓታት በፊት ነው።

ይህ በእንዲህ እንዳለ በሩሲያ የታገዙ የሦሪያ መንግሥት ጦር አውሮፕላኖች ምሥራቅ ጎታን ዛሬ በተከታታይ ለ6ኛ ቀን ሲደበድቡ ውለዋል። በጥቃቱ በትንሹ 5ሰዎች መገደላቸውን የተቃዋሚ መሪዎችና ጦርነቱን በቅርብ የሚከታተሉ ወገኖች አስታውቀዋል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG