ዋሺንግተን ዲሲ —
የቱርክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የሳዑዲ ተወልጅ ጋዜጠኛ ዣማል ኻሾግዢ አገዳደልን አስመልክቶ ከሚመረምረው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የፍርድ ጠቢብ ጋር ዛሬ ተገናኝተው ተነጋገረዋል። ቱርክ ዓለምቀፍ ምርመራ እንዲካሄድበት እየጠየቀች ነው።
የመንግሥታቱ ድርጅት ልዩ መርማሪ አጀንስ ካላማንደር እስከ ቅዳሜ ድረስ ቱርክ በመቆየት የኢስታምቡል ዋና ዐቃቤ ህግ ከሚገኑባቸው ባለሥልጣኖች ጋር ተገናኝተው ይነጋገራሉ።
አጀንስ ካላማንደር ቱርክ ካሉት የሳዑዲ አረብያ አምባሳደር ጋር ለመነጋገርና ምርመራውን ለማካሄድ ሳዑዲ አረብያም ጭምር ለመሄድ ላቀረቡት ጥያቄ የሳዑዲ አረብያ ባለሥልጣኖች ምላሽ ሰጥተው እንዳሆነ ማራጋገጫ አልሰጡም።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ