በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኢራን ተቃዋሚዎችን መግደሏን የተመድ አወገዘ


የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ ጉዳዮች ኃላፊ ቮልከር ቱርክ
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ ጉዳዮች ኃላፊ ቮልከር ቱርክ

ኢራን በተቃውሞ የተሳተፉ ሰዎችን በሞት መቅጣቷ ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ሕግን የጣሰ ነው ሲሉ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ ጉዳዮች ኃላፊ ቮልከር ቱርክ ዛሬ አስታወቁ።

“የሕግ ሂደትን እንደመሣሪያ በመጠቀም በተቃውሞ የተሳተፉ ሰዎችን በሞት መቅጣት በመንግሥት እንደሚፈጸም ግድያ ይቆጠራል” ብለዋል ቮልከር ቱርክ።

ሂጃብ በሚገባ አልተከናነብሽም በሚል ባለፈው መስከረም የ22 ዓመቷ ማህሳ አሚኒ በፖሊስ እጅ ከሞተች ወዲህ በኢራን ከፍተኛ ተቃውሞ ሲነሳ፣ እስከ አሁን የኢራን ከፍተኛ ፍ/ቤት 4 በተቃውሞ የተሳተፉ ሰዎች ላይ የሞት ቅጣትን አስተላልፎ ተፈጻሚ ሆኗል።

የኢራን ፍ/ቤት ግለሰቦቹ የጸጥታ ኃይሎችን በማጥቃታቸው ተከሰዋል ቢልም፣ የተመድ ግን በጥድፊያና በዝግ የተደረገውን የፍርድ ሂደት ተችቷል።

የተመድ የሰብዓዊ መብት ቢሮ አክሎም 2 የማይቀሩ የሞት ቅጣቶች በቅርቡ እንደሚፈጸሙ መረጃ አለኝ ብሏል።

ኢራን የሞት ቅጣቱን አሁኑኑ አቁማ ለሕዝቡ ጥያቄ መልስ እንድትሰጥ ቮልከር ቱርክ ጥሪ አቅርበዋል።

XS
SM
MD
LG