በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ተመድ - በየመን ላይ የተደነገገው የጦር መሳሪያ ማዕቀብ

በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የፀጥታ ምክር ቤት ኢራንን በየመን ሁቲ አማፁያን ላይ የተደነገገውን የጦር መሳሪያ ማዕቀብ በመጣስ የሚወነጅላት ውሳኔ እንዳይተላለፍ ሩስያ ማደናቀፏ ተዘግቧል።

በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የፀጥታ ምክር ቤት ኢራንን በየመን ሁቲ አማፁያን ላይ የተደነገገውን የጦር መሳሪያ ማዕቀብ በመጣስ የሚወነጅላት ውሳኔ እንዳይተላለፍ ሩስያ ማደናቀፏ ተዘግቧል።

ብሪታንያ ባረቀቀችው ውሳኔ ላይ ትናንት ሰኞ ድምፅ ሲሰጥ ሩስያ ድምፅ በመሻር ሥልጣንዋ የጣለችው ሲሆን ቦሊቪያም ሩስያን ተከትላ ውሳኔውን ተቃውማ ድምፅ ሰጥታለች። ቻይናና ካዛክስታን ደግሞ ድምፅ ተአቅቦ አድርገዋል።

ይህንኑ ተከትሎ ምክር ቤቱ በየመን ላይ የተደነገገው ማዕቀብ በአንድ ዓመት እንዲራዘም እና ማዕቀቡ ሥራ ላይ መዋሉን የሚከታተለው የኢክስፐርቶች ኮሚቴ ሥራውን ኣንዲቀጥል የሚጠይቅ በሩስያ የቀረበ ውሳኔ በሙሉ ድምፅ አሳልፉዋል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG