በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ተመድ እስራኤል በጋዛ ያካሄደችው የአየር ድብደባ 'የጦርነት ህግን' ጥሶ ሊሆን ይችላል አለ


በደቡባዊ ጋዛ ሰርጥ በራፋህ አካባቢ የእስራኤል የቦምብ ጥቃት የሚሸሹ ፍልስጤማውያን
በደቡባዊ ጋዛ ሰርጥ በራፋህ አካባቢ የእስራኤል የቦምብ ጥቃት የሚሸሹ ፍልስጤማውያን

እስራኤል በጋዛ ላይ ያካሄደችው የአየር ድብደባ "መሠረታዊ የጦርነት ሕግ መርሆዎችን በተጋጋሚ ጥሶ ሊሆን ይችላል" ሲል የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብዓዊ መብቶች ቢሮ አስታወቀ።

የመንግስታቱ ድርጅት ቢሮ ዛሬ ረቡዕ ይፋ ያደረገው ሪፖርት፣ ባለፈው ዓመት ከጥቅምት እስከ ታህሳስ ወር ባሉት፣ በጋዛ ጦርነት በተከፈተባቸው ሳምንታት በእስራኤል መከላከያ ሰራዊት የተካሄዱትን ስድስት የአየር ድብደባዎች መርምሯል።

የመኖሪያ ህንፃዎችን፣ ትምህርት ቤቶችን፣ የገበያ ስፍራዎችን እና የስደተኛ መጠለያ ጣቢያዎችን ኢላማ ባደረጉት የአየር ጥቃቶችም ከ200 የሚበልጡ ሰዎች መሞታቸውን የሰብዓዊ መብቶች ቢሮ ማረጋገጡን ሪፖርት ገልጿል።

መሠረታዊ የጦርነት ሕግ መርሆዎችን በተጋጋሚ ጥሶ ሊሆን ይችላል"

የተባበሩት መንግሥታት የሰብአዊ መብት ከፍተኛ ኮሚሽነር ቮልከር ቱርክ በሪፖርቱ ላይ በሰጡት አስተያየት፣ እስራኤል በጋዛ ላይ ባካሄደችው የቦምብ ጥቃት ዘመቻ በፍልስጤም ሲቪሎች እና በሐማስ ተዋጊዎች መካከል “ልዩነት ለማድረግ” ምንም አይነት ጥረት አለማድረጓን ተናግረዋል።

እስራኤል በአካሄደቻቸው ስድስቱ ጥቃቶች ከ113 ኪሎ ግራም እስከ 907 ኪሎግራም የሚመዝኑ ከባድ ቦምቦችን መጠቀሟን ሪፖርቱ ጨምሮ ገልጿል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG