በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኢትዮጵያ፣ የኤርትራና የሶማሊያ ውጪ ጉዳይ ሚኒስትሮች የጂቡቲ ጉብኝት ተመድ አደነቀ

የኢትዮጵያ፣ የኤርትራና የሶማሊያ ውጪ ጉዳይ ሚኒስትሮች ጂቡቲን መጎብኘታቸውና ከሀገሪቱ አቻቸው ጋርም መገናኘታቸው፣ ለአፍሪካ ቀንድ ሀገሮች ሰላምና መረጋጋት ከፍተኛ አስተዋፅዖ እንዳለው፣ የተመድ ዋና ጸሓፊ አስታወቁ።

የኢትዮጵያ፣ የኤርትራና የሶማሊያ ውጪ ጉዳይ ሚኒስትሮች ጂቡቲን መጎብኘታቸውና ከሀገሪቱ አቻቸው ጋርም መገናኘታቸው፣ ለአፍሪካ ቀንድ ሀገሮች ሰላምና መረጋጋት ከፍተኛ አስተዋፅዖ እንዳለው፣ የተመድ ዋና ጸሓፊ አስታወቁ።

የኢትዮጵያ፣ የኤርትራና የሶማሊያ ውጪ ጉዳይ ሚኒስትሮች ወደ ጁቡቲ ያመሩት ባለፈው ሐሙስ ሲሆን፣ ጂቡቲን ጨምሮ አራቱ ሀገሮች ለሰላምና ለአንድነት በጋራ ለመሥራት ከሥምምነት መድረሳቸው ለአፍሪካ ቀንድና ለሌላውም አካባቢ አዎንታዊ ምሳሌ መሆኑን ድርጅቱ ዋና ጸሓፊ ገልፀዋል።

ዋና ጸሓፊው አክለውም፣ ይህን በአራቱ አገሮች መካከል የተደረሰውን የሰላም ስምምነት ለማጠናከር ለሚፈልጉ አገሮች፣ ድርጅቱ ድጋፉን እንደማነፍጋቸው ቀደም ያለውን ቃል አጠናክረዋል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG