በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በሄይቲ የኃይል ስምሪት የጸጥታው ም/ቤት ዛሬ ውሳኔ እንደሚያሳልፍ ይጠበቃል


የተደራጁ ወንጀለኛ ቡድኖች፣ የመዲናዋን ፖርት ኦ ፕሪንስ መጠለያ የሚገኙ ሄይቲያን
የተደራጁ ወንጀለኛ ቡድኖች፣ የመዲናዋን ፖርት ኦ ፕሪንስ መጠለያ የሚገኙ ሄይቲያን

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የጸጥታው ምክር ቤት፣ በተደራጁ የወንጀል ቡድኖች እየታመሰች ባለችው ሄይቲ የሚገኘውን ፖሊስ ለማገዝ፣ ዓለም አቀፍ ኃይል በሚላክበት ጉዳይ ላይ፣ ዛሬ ሰኞ ድምፅ እንደሚሰጥ ይጠበቃል።

ኬንያ፣ ከተለያዩ ሀገራት የተውጣጡ አንድ ሺሕ የፖሊስ አባላትን ለመምራት ፈቃደኝነቷን አሳይታለች፡፡ ባሃማስ፣ ጃማይካ፣ አንቲጓ እና ባርቡዳ በበኩላቸው፣ የጸጥታ አባላትን ለመላክ ተስማምተዋል።

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት፣ የገንዘብ እና የአቅርቦት ድጋፍ እንደሚያደርግ አስታውቋል።

በቅርቡ በተደረገው የመንግሥታቱ ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ ላይ የተናገሩት የሄይቲ ጠቅላይ ሚኒስትር ኤሪየል ሄንሪ፣ በአገሪቱ እየተባባሰ የመጣው የወንጀል ቡድኖች ኹኔታ ሰብአዊ ቀውስ በመፍጠሩ፣ የጸጥታው ም/ቤት አስቸኳይ ውሳኔ እንዲያሳልፍ ጠይቀዋል።

በሄይቲ፣ የተደራጁ ወንጀለኛ ቡድኖች፣ የመዲናዋን ፖርት ኦ ፕሪንስ በርካታ ክፍሎች ተቆጣጥረው፥ ግድያ፣ እገታ፣ ሕገ ወጥ የሰዎች ዝውውር እና ጾታዊ ጥቃት በመፈጸም ላይ እንደሚገኙ፣ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጨምረው ገልጸዋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG