በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ባንኪ ሙን ተሰናበቱ፤ አንቶኒዮ ጉቴሬስ ገቡ


ባን ኪ ሙን እና አንቶኒዮ ጉቴሬስ
ባን ኪ ሙን እና አንቶኒዮ ጉቴሬስ

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ላለፉት አጭር ዓመታት በዋና ፀሐፊነት ያገለገሉት ባን ኪ ሙን ዛሬ ታኅሣሥ 21/2009 ዓ.ም ተሰናብተዋል፡፡

ድርጅቱን ለሁለት የአስተዳደር ዘመናት የመሩት ደቡብ ኮሪያዊው ባን ቀደም ሲል የሀገራቸው የውጭ ጉዳይና የንግድ ሚኒስትር ሆነው አገልግለዋል፡፡

በእርሳቸው እግር ዘጠነኛው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ እንዲሆኑ የተመረጡት አንቶኒዮ ጉቴሬስ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የስደተኞች ጉዳዮች ከፍተኛ ኮሚሽነር፣ ቀደም ሲልም 114ኛው የፖርቹጋል ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው አገልግለዋል፡፡

ተሰናባቹ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በዋና ፀሐፊ ባን ኪ ሙን
ተሰናባቹ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በዋና ፀሐፊ ባን ኪ ሙን

​የ67 ዓመቱ አንቶኒዮ ማኑዪል ዴ ኦሊቬራ ጉቴሬስ የሀገራቸው ሶሻሊስት ፓርቲ ዋና ፀሐፊና የሶሻሊስት ኢንተርናሽናልም ፕሬዚዳንት ነበሩ፡፡

አንቶኒዮ ጉቴሬስ ምክትላቸው እንዲሆኑ የመረጧቸው ናይጀሪያዊቱን የአካባቢ ጥበቃ ሚኒስትር አሚና መሐመድን ነው፡፡

ናይጀሪያዊቷ የአካባቢ ጥበቃ ሚኒስትር መጭዋ የመንግሥታቱ ድርጅት ምክትል ዋና ፀሐፊ አሚና መሐመድ
ናይጀሪያዊቷ የአካባቢ ጥበቃ ሚኒስትር መጭዋ የመንግሥታቱ ድርጅት ምክትል ዋና ፀሐፊ አሚና መሐመድ

ስለተባበሩት መንግሥታት ድርጅት እና ስለ አንቶኒዮ ጉቴሬስ በኦሃዩ ዩኒቨርስቲ የፖለቲካ ሳይንስ ፕሮፌሰሩ ኮ/ር ብሩክ ኃይሉ ትንታኔ ይሰጣሉ፣ ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡት፡፡

ባንኪ ሙን ተሰናበቱ፤ አንቶኒዮ ጉቴሬስ ገቡ
please wait

No media source currently available

0:00 0:19:32 0:00

XS
SM
MD
LG