75ኛው የተመድ ጉባዔ
193 የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አባል ሃገሮች መሪዎች በድርጅቱ የ75 ዓመት ዕድሜ ለመጀመሪያ ጊዜ፣ የዓመታዊ ጠቅላላ ጉባዔው መክፈቻ ንግግራቸውን በአካል ሳይገኙ አስቀድሞ በተቀዳ መልዕክቶቻቸውን እያሰሙ ናቸው። ኒው ዮርክ በሚገኘው በግዙፉ የመንግሥታቱ ድርጅት የጠቅላላ ጉባዔ አዳራሽ በአካል ተገኝተው ንግግሮቹን የሚከታተሉት ከእያንዳንዱ አባል ሃገር አንድ ብቻ ተወካይ ሲሆን ከአውሮፓ ህብረት እና በታዛቢ አባል የሆነችው የፍልስጥኤም ተወካይም ይገኛሉ።