በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ትረምፕ ኢራንን “ከዓለም ዋናዋ የአሸባሪዎች ደጋፊ”አሏት

ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ ኢራንን “ከዓለም ዋናዋ የአሸባሪዎች ደጋፊ” ብለዋታል። ከሦሰት ዓመታት በፊት ከኢራን ጋር የተደረገውን የኑክሌር ሥምምነት መንቀፉንም ቀጥለዋል። ዩናይትድ ስቴትስ በያዝነው ዓመት ቀደም ሲል ከሥምምነቱ መውጣትዋ የሚታወቅ ነው።

ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ ኢራንን “ከዓለም ዋናዋ የአሸባሪዎች ደጋፊ” ብለዋታል። ከሦሰት ዓመታት በፊት ከኢራን ጋር የተደረገውን የኑክሌር ሥምምነት መንቀፉንም ቀጥለዋል። ዩናይትድ ስቴትስ በያዝነው ዓመት ቀደም ሲል ከሥምምነቱ መውጣትዋ የሚታወቅ ነው።

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የፀጥታ ምክክር ቤት ከድርጅቱ ጠቅላል ጉባዔ ጎን የኑክሌር መሳርያ መሥፋፋትን ስለመገደብ ያደረገውን ስብሰባ የመሩት ፕሬዚዳንት ትረምፕ “የኢራን የኃይል ተጠቃሚንት ባህሪ የጨመረው” የኑክሌር ሥምምነት ከተፈረመ በኋላ ነው ብለዋል።

“እንዲህ ዓይነት ባህሪ ያለው መንግሥት ኑክሌር መሳርያ እንዲኖረው መፈቀድ የለበትም ካሉ በኋላ አሜሪካ በቴህራን ላይ ከባድ ማዕቀብ ትጥላለች በማለት አስጠንቅቀዋል።

የፀጥታው ምክር ቤት ስብሰባ የተደረገው ትረምፕ ለተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባዔ ባደረጉት ንግግር “የኢራን መንግሥት በኃይል ተጠቃሚነት ባህሪው እስከቀጠለ ድረስ መገለል ይኖርበታል” ባሉ ማግሥት ነው።

የኢራን ፕሬዚዳንት ሀሰን ሩሃኒ በበኩላቸው በጠቅላላው ጉባዔ ባደረጉት ንግግር ማንንም ሀገር በግድ ወደ ድርድር ጠረጴዛ ለማቅረብ አይቻልም ብለዋል። ሩሃኒ አያያዘውም ኢራን በባራክ ኦባማ አስተዳደር ወቅት የነበሩትን ፖሊሲዎች ከምትጥስ ዩናይትድ ስቴትስ ጋር እንዴት ሥምምነት ውስጥ ልትገባ ትቻላለች? በማለት ጠይቀዋል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG