በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የጋዛ ጦርነቱ የረሃብ ቸነፈር ሥጋት


ፎቶ ፋይል፦ ፍልስጤማውያን በራፋህ በጋዛ ሰርጥ ለምግብ ተሰልፈው እአአ ታኅሳስ 21/2023
ፎቶ ፋይል፦ ፍልስጤማውያን በራፋህ በጋዛ ሰርጥ ለምግብ ተሰልፈው እአአ ታኅሳስ 21/2023

በጋዛ ሰርጥ ያለው እጅግ አደገኛ ሁኔታ አሁንም እንደቀጠለ መሆኑን በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የተደገፈው የምግብ ዋስትና ሪፖርት አስታወቀ። የእስራኤል እና የሐማስ ጦርነት እስከቀጠለ እና የሰብዓዊ ረድኤት አቅርቦት እስከተገደበ ድረስ በመላዋ ጋዛ የረሐብ ቸነፈር አደጋው አይቀሬ መሆኑን ሪፖርቱ አስገንዝቧል።

በእንግሊዝኛ የምህጻር መጠሪያው አይፒሲ የተባለው የተቀናጀ የምግብ ዋስትና ምዕራፎች ትንተናው ሪፖርት ወደ ግማሽ ሚሊዮን የሚሆኑ የጋዛ ነዋሪዎች የረሐብ ቸነፈር አፋፍ ላይ መሆናቸውን እና 745, 000 ሰዎች አጣዳፊ ረሃብ ደረጃ ላይ መሆናቸውን አመልክቷል።

የሪፖርቱ አቅራቢዎች አክለውም ከጋዛ ሕዝብ 96 ከመቶው ማለትም 2 ነጥብ 15 ሚሊዮን ሰዎች በአሁኑ ወቅት በከባድ የምግብ ዋስትና እጦት ችግር ላይ እንዳሉና ይህ ሁኔታም እስከመጪው መስከረም ወር የሚቀጥል መሆኑን ተናግረዋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG