በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ጉዞ ከልካዩ ኮቪድ-19 ያልገደበው ስደት


ተፈናቃዮች በመቀሌ በሚገኙ ት/ቤቶች ተጠልለው ይገኛሉ።
ተፈናቃዮች በመቀሌ በሚገኙ ት/ቤቶች ተጠልለው ይገኛሉ።

“አሁን ከሰው ልጅ ቁጥር ከአንድ በመቶ በላይ የሚሆነው ከቀዬው ለመፈናቀል ከተገደደበት ደረጃ ላይ ደርሰናል። በዚህም እጅግ ከሚያስደምሙኝ አሃዞች ውስጥአርባ በመቶው ህጻናት የመሆናቸው ዕውነታ ነው።” በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽነር ፊሊፖ ግራንዲ፡፡

ባለፈው ዓመት በጦርነት፣ በግጭት፣ በደረሱባቸው የሰብአዊ መብት ጥሰቶች ተገፍተው ቀያቸውን ጥለው ለመሰደድ የተገደዱ ተፈናቃዮች ቁጥር 82.4ሚሊዮን መድረሱን የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ድርጅት/ዩኤንኤችሲአር/ አስታወቀ። ይህም አሃዝ ከዚያ አንድ ዓመት በፊት እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ2019 ከተመዘገበው ጋር ሲነፃፀር በአራት በመቶ የሚበልጥ መሆኑን ዘገባው ጨምሮ አመልክቷል፡፡

ድርጅቱ የስደተኞችን አሃዝ እና የፍልሰት ገጽታ የሚያሳየውን ዓመታዊ ሪፖርቱን በዛሬው ዕለት ነው ይፋ ያደረገው። ቀያቸውን ጥለው ለመሰደድ የሚገደዱ ሰዎች ቁጥር ከዓመት ወደ ዓመት እየጨመረ ሲመጣ፣የአሁኑ በተከታታይ ለዘጠነኛ ዓመት መሆኑ ነው፡፡ ሌላው ቀርቶ ዓለምን ያዳረሰው የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ፤ አለያም በዚሁ ሳቢያ ተጥሎ የነበረው የእንቅስቃሴ ገደብ እና የድንበሮች መዘጋት እንኳን ሰዎች ጦርነትና የጭካኔ አድራጎቶችን በመሸሽ ሕይወታቸውን ለማትረፍ የሚያደርጉትን ስደት አላስቆማቸውም።

ቁጥሩ ከ82 ሚሊዮን በላይ የሚደርስ ሰው መኖሪያውን ጥሎ ለመሰደድ ሲገደድ ከዚህም ውስጥ 26.4 ሚሊዮኑ ከለላ ፍለጋ ዓለም አቀፍ ድንበሮችን ለመሻገር ግድ የሆነበት ነው፡፡ ከቀረውም ውስጥ አብዛኛው በግጭትና በሁከት ሳቢያ የአገር ውስጥ ተፈናቃይነት ዕጣው የሆነ ነው፡፡

ሙሉ ዘገባውን ከዚህ ያድምጡ።

ጉዞ ከልካዩ ኮቪድ-19 ያልገደበው ስደት
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:05 0:00


XS
SM
MD
LG