በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ከዳርፉር ክልል ወደ ቻድ የሚሻገሩ ስደተኞች ቁጥር እየጨመረ መሆኑን ተመድ አስታወቀ


ፎቶ ፋይል፦ ግጭት በመሸሽ ቻድ የተሰደዱ ሱዳናውያን በቻድ ኩፍሮም በጠለያ ጣቢያ
ፎቶ ፋይል፦ ግጭት በመሸሽ ቻድ የተሰደዱ ሱዳናውያን በቻድ ኩፍሮም በጠለያ ጣቢያ

በሱዳን ሶስት ወራትን ያስቆጠረውን ግጭት በመሸሽ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ጎረቤት ወደምትገኘው ማዕከላዊ አፍሪካዊቷ ሀገር ቻድ እየተሰደዱ መሆናቸውን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የዓለም ምግብ ፕሮግራም አስታውቋል። የዓለም አቀፉ ሰብዓዊ ተቋም ኃላፊም በሱዳን ያለውን ሁኔታ "እጅግ በጣም ጭካኔ የሞላበት" የእርስ በእርስ ጦርነት ሲሉ ገልፀውታል።

የዓለም ምግብ ፕሮግራም ዛሬ ባወጣው መግለጫ፣ ባለፈው ሳምንት ብቻ፣ ከሱዳን ዳርፉር ክልል የተነሱ 20 ሺህ ሰዎች በቻድ ድምበር ላይ ወደምትገኘው አድሬ የተሰኘች ትንሽ ከተማ መግባታቸውን ገልጿል።

የቆሰሉ እና የፈሩ ሰዎች ልጆቻቸውን በእጃቸው እና ልብሳቸውን በጀርባቸው አድርገው ድንበሩን አቋርጠው እየሮጡ ነው"

በሱዳን ያለው ግጭት ጎሳን መሰረት እያደረገ መምጣቱን ተከትሎ እየሸሹ ያሉ ሰላማዊ ዜጎች ሆን ተብለው ዒላማ ይደረጋሉ የሚሉ ሪፖርቶች እየወጡ ባሉበት ወቅት፣ ከዳርፉር ወደ ቻድ የሚገቡት ስደተኞች አብዛኞቹ በጠና የቆሰሉ መሆናቸውን የምግብ ተቋሙ መግለጫ ጨምሮ አመልክቷል። ወደ ቻድ ከሚገቡት ህፃናት 10 በመቶ ያክሉም የተመጣጠነ የምግብ እጥረት አለባቸው ብሏል።

"የቆሰሉ እና የፈሩ ሰዎች ልጆቻቸውን በእጃቸው እና ልብሳቸውን በጀርባቸው አድርገው ድንበሩን አቋርጠው እየሮጡ ነው" ያሉት በቻድ የዓለም ምግብ ፕሮግራም ኃላፊ ፒየር ሆኖራት፣ "ከአደጋ የሚጠበቁበት፣ ደህንነት የሚሰማቸው ቦታ እና ሰብዓዊ እርዳታ ይፈልጋሉ" ብለዋል።

በሱዳን ጦር ሰራዊት እና ፈጥኖ ደራሽ ድጋፍ ሰጪ ኃይሎች መካከል በሚያዚያ ወር ጦርነት ከተነሳ ጀምሮ ከ230 ሺህ በላይ ስደተኞች እና 38 ሺህ ተመላሾች ወደ ቻድ መግባታቸው ተመልክቷል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG