በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ተመድ 129 ኢትዮጵያዊያን ፍልሰተኞችን ከየመን ወደ አገራቸው መለሰ


ፎቶ ፋይል - ኢትዮጵያውያን ፍልሰተኞች በራስ አል አራ፣ ላህጅ፣ የመን ዳርቻ።
ፎቶ ፋይል - ኢትዮጵያውያን ፍልሰተኞች በራስ አል አራ፣ ላህጅ፣ የመን ዳርቻ።

የተባበሩት መንግሥታት በጦርነት ውስጥ ባላችው የመን መውጫ ያጡ 129 ፍልሰተኞችን ወደ አገራቸው ኢትዮጵያ መመለሱን አስታወቀ፡፡

ድርጅቱ በአማጽያን ቁጥጥር ስር ካለቸው የየመን ዋና ከተማ ሰንዓ ስደተኞቹን ለመመለስ የመጀመሪያውን በረራውን ያካሄደው ትናንት ማክሰኞ መሆኑ ተገልጿል፡፡

የተባበሩት መንግሥታት የፍልሰተኞች ድርጅት በዚህ ዓመት ከ1ሺ800 በላይ ፈቃደኛ የሆኑ ፍልተኞችን ከየመን ወደ የአገራቸው መመለሱን አስታውቋል፡፡ አብዛኞቹ ከአፍሪካ ቀንድ የፈለሱ መሆናቸውንም ዓለም አቀፉ ድርጅቱ አመልክቷል፡፡

የየመኑ አውዳሚ ጦርነት የተጀመረው እኤአ በ2014 በኢራን የሚደገፉ የሁቲ አማጽያን ሰነዓን ከተቆጣጠሩ በኋላ መሆኑ ተነግሯል፡፡

ከዓመት በኋላም በሳዑዲ አረቢያ የሚመራው ጥምር ጦር ዓለም አቀፍ እውቅና ያለው መንግሥት በሥፍራው ለመመለስ በሚል ጣልቃ መግባት መጀመሩን የአሶሴይትድ ፕሬስ ዘገባ አመልክቷል፡፡

አሁንም ከየመን ውስጥ መውጫ አጥተው ያሉ ወደ 43ሺ800 የሚደርሱ አብዛኞቹ ከምስራቅ አፍሪካ የሆኑ ፍልሰተኞች አሉ ተብሎ እንደሚገመት ተገልጿል፡፡

XS
SM
MD
LG