በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በኢትዮጵያ እየተባባሰ የመጣው የሰብዓዊ ሁኔታ እንዳሳሰበው ተመድ አስታወቀ


በሰሜን ኢትዮጵያ በድርቅ በተጠቁ ክልሎች፤ ማለትም፣ በአፋር አማራ እና ትግራይ እንዲሁም በኦሮሚያ ክልል “እየተበላሸ በመምጣት ላይ ነው” ሲል የገለጸው የሰብዓዊ ሁኔታ እንዳሳሰበው የተመድ የሰብዓዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ቢሮ አስታውቋል።

የተመድ ቃል አቀባይ የሆኑት ስቴፋን ዱጃሪክ ዛሬ በሰጡት መግለጫ፣ ድርቁ በመባባሱ ምክንያት በተጠቀሱት ክልሎች ለሚገኙ 4 ሚሊዮን ለሚሆኑ ሰዎች የሚሰጠው ምላሽ መጠናከር እንዳለበት ተናግረዋል።

በርካታ እና ተደራራቢ ቀውሶች፣ ሰዎች በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት የሚመጡ ችግሮችን መቋቋም እንዳይችሉ ማድረጉን የጠቀሱት ቃል አቀባዩ፣ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች ለከፋ ሁኔታ ተጋላጭ እንዲሆኑ አድርጓል ብለዋል።

ከፍተኛ የገንዘብ እጥረት ባለበት እንዲሁም በአማራ እና በኦሮሚያ ክልል ግጭቶች ባሉበትም ሁኔታ ቢሆን፣ ተመድ እና አጋሮቹ የመንግስትን ጥረት በመደገፍ ላይ መሆናቸውን ቃል አቀባዩ ገልጸዋል።

ባለፈው የፈረንጆች ዓመት 12 ሚሊዮን ለሚሆኑ ሰዎች ተመድ እና አጋሮቹ ርዳታ መለገሳቸውንና 4 ቢሊዮን ዶላር እንደሚያስፈልገው ለታቀደው ሰብዓዊ ሥራ፣ ሊገኝ የተቻለው ገንዘብ ግን አንድ ሶሶተኛ የሚሆነው ብቻ እንደሆነ ተመልክቷል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG