በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኤርትራ ስለ ሶማልያ በሚደረጉ ስብሰባዎች እንዳትገኝ መታገድዋን አቶ የማነ ገብረአብ ገለጹ



ኤርትራ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የጸጥታ ምክር ቤት ፊት ቀርባ ጉዳይዋን ለማብራራት ባለፈው ሰኔ ወር በጠየቀችው መሰረት ትላንት ማክሰኞ የኢትዮጵያ፣ የሶማልያ፣ የኬንያና የኡጋንዳ ተወካዮች በተገኙበትጉድይዋን ኒው ዮርክ ከተማ በሚገኘው የጸጥታ ምክር ቤት ለማቅረብ ችላለች።ኤርትራ ብቻዋን ነበር ጉዳይዋን ለማቅረብ የፈለገቸው። ይሁና እንደ ኤርትራ አባባል በ United States ጫና ኢትዮጵያና ሌሎችም ሀገሮች ሊገኙ ችለዋል።

" ኤርትራ ስለ ሶማልያ አስተዋጽኦ ልታደርግ የምትችል ሀገር ሆና ሳለ በስብሰባዎቹ እንድንሳተፍ አልተፈቀደም። አላማው የኤርትራን አንደበት ለመሸበብና በሌለችበት ለማጥቃት ነው።” ሲሉ የኤርትራ መንግስት የፖለቲካ ጉዳዮች ሃላፊ አቶ የማነ ገብረአብ አማረዋል።

በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የኢትዮጵያ አምባሳደር ዶክተር ተቀዳ አለሙ ደግሞ "ኤርትራ ለሶማልያ ሰላም እየሰራች አይደለም። ሰላም እንዳይሰፍን ነው እያደረገች ያለቸው። ከዐል ሸባብ ጋር ያላቸው ግንኙነት እንደቀጠለ ነው። ናይሮቢ ከሚገኘው ኤምባሲያቸው በየወሩ ከ 80,000 ዶላሮች በላይ ለዐል ሸባብ ባለስልጣኖች ይቀርባል የሚል የቁጥጥር ቡድኑ ሪፖርት አለ" ሲሉ አምባሳደር ተቀዳ አለሙ ጠቅሰው ሁኔታው ይህ ሆኖ ሳለ እንዴት ነው ለሶማልያ ሰላም አስተውጽኦ ሊያደርጉ የሚችሉት? ብለዋል።

XS
SM
MD
LG