በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ተመድ ስለ ኢትዮጵያና ኤርትራ

ፎቶ ፋይል
ፎቶ ፋይል

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ፀኃፊ የኤርትራ ከፍተኛ ልዑካን ኢትዮጵያ መግባታቸው የሁለቱን ሀገሮች ግንኑነት ወደ መደበኘው እንዲመለስ ለማድረግ የሚያስችል የመጀመርያ ተጨባጭ ዕርምጃ ነው ማለታቸው ተገልጿል።

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ፀኃፊ የኤርትራ ከፍተኛ ልዑካን ኢትዮጵያ መግባታቸው የሁለቱን ሀገሮች ግንኑነት ወደ መደበኘው እንዲመለስ ለማድረግ የሚያስችል የመጀመርያ ተጨባጭ ዕርምጃ ነው ማለታቸው ተገልጿል።

ዋናው ፀኃፊ አንቶንዮ ጉተሬዥ አያይዘውም በሁለቱ ሀገሮች መካከል ሰፍኖ የቆየውን ውጥረት ለማርገብና ለተራዘመ ጊዜ ለቀጠለው ጠባቸው መፍትሄ ለማግኘት የሚደረገው ዲፕሎማስያዊ ጥረት በመላው ክልል አዎንታዊ ተፅዕኖ ይኖረዋል ማለታቸውን በኢትዮጵያና ኤርትራ ጉዳይ ቃል አቀባያቸው ባወጡት መግለጫ ጠቁመዋል።

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ሁለቱ ሀገሮች የድንበሩን ውሳኔ በሚተገበሩበት ወቅትም ሆነ በማንኛውም የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዕርዳታ ያሰፈልገዋል ብለው በሚያምኑት ነገር ሁሉ ለመርዳት ዝግጁ መሆኑንም ዋናው ፀኃፊ በድጋሚ ገልፀዋል ይላል መግለጫው።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG