በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኤርትራ የሽብርተኛነት እንቅስቃሴ ኢትዮጵያንና የአከባቢ ሀገሮችን እያሳሰበ ነው ብለዋል አምባሳደር ተቀዳ አለሙ


ኤርትራ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የጸጥታ ምክር ቤት ፊት ቀርባ ጉዳይዋን ለማብራራት ባለፈው ሰኔ ወር በጠየቀችው መሰረት ባለፈው ማክሰኞ የኢትዮጵያ፣ የሶማልያ፣ የኬንያና የኡጋንዳ ተወካዮች በተገኙበት ጉድይዋን ኒው ዮርክ ከተማ በሚገኘው የጸጥታ ምክር ቤት ለማቅረብ መቻልዋን ባለፈው ሳምንት ባቀረብናቸው ተከታታይ ቅንብሮች መግለጻችን ይታወሳል።

በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የኢትዮጵያ አምባሳደር ዶክተር ተቀዳ አለሙ ኤርትራ በኢትዮጵያ ልታደረሰው አቅዳ ነበር ስላሉት የሽብርተኛነት ተግባር ሲያብራሩ "የአፍሪቃ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ ሊካሄድ ዝግጅት ይደረግ በነበረበት ወቅት የገበያ ቦታዎች፣ መንግስታዊ ተቋማትና የስብሰባ አካባቢዎች በቦምብ ፍንዳታዎች እንዲጎዱ ለማድረግ ነብር አላማዋ" ብለዋል።

የኤርትራ መንግስት የፖሊቲካዊ ጉዳዮች ሀላፊ አቶ የማነ ገብረአብ ደግሞ ስለ ኤርትራ ራዕይ ሲናገሩ "የኛ ራዕይ በአፍሪቃ ቀንድ ሁሉንም የሚያቅፍ የመልካም ጉርብትና የኢኮኖሚ መረዳዳትና የሽርክና ቀጠና እንዲሆን ስለምናደርገው ጥረት ገልጸናል" ብለዋል።

XS
SM
MD
LG