በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የተባበሩት መንግሥታቱ ድርጅት የኤርትራውያን ስደተኞች ጉዳዮች አሳስቦኛል አለ።


UNHCR
UNHCR

በሰሜን ኢትዮጵያ የትግራይ ክልል በውጊያውምክንያት ካምፖቻቸውን ጥለው የሸሹ ኤርትራውያን ስደተኞች በግድ ወደካምፖቻቸው እንዲመለሱ እየተደረገ መሆኑ አሳስቦኛል ሲል የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ተናገረ።

የመንግሥታቱ ድርጅት የስደተኞች ከፍተኛ ኮምሽነር በብዙ መቶዎች የሚቆጠሩ ስደተኞች በአውቶቡስወደ ስደተኛ ጣቢያዎቹ እየተወሰዱ ስለመሆኑ ሪፖርት ደርሶናል ብሏል።

የኢትዮጵያ መንግሥት “የመከላከያ ኃይላችን በትግራይ ክልል የሕወሃት ኃይሎች ላይ ድል ተቀዳጅቷል” ስለሆነም ስደተኞቹ ወደካምፖቻቸው ቢመለሱ የሚያሰጋ ነገር አይኖርም ማለቱን ዜናው ጠቅሱዋል።

የመንግሥታቱ ድርጅት የስደተኞች ከፍተኛ ኮምሽነር ፌሊፔ ግራኒዲ ትናንት ዓርብ ባወጡት መግለጫቸው የድርጅቱ የረድዔት እና ሌሎችም ድርጅቶች ወደክልሉ ለመግባት በተከለከሉበት ሁኔታ ስደተኞቹ መመለሳቸው ያሳስበናል ብለዋል።

ዘጠና ስድስት ሺህ ኤርትራውያን ስደተኞች በተጠለሉባቸው የስደተኛ ካምፖች የምግብ ዕጥረት አለ ብለን እናምናለን ያሉት የረድዔት ድርጅቶች በአንዳንዶቹ የትግራይ አካባቢዎች ውጊያ አሁንም እንዳለ የሚገልጹ ሪፖርቶች አሳስበውናል ሲሉም አስታውቀዋል።

የዩ ኤን ኤች ሲ አር ከፍተኛ ኮምሽነር ፌሊፔ ግራንዲ በመግለጫቸው የኢትዮጵያ መንግሥት የመንግሥታቱ ድርጅት የረድዔት መስሪያ ቤቶች እና አጋሮቻቸው “ወድ ክልሉ ደህንንታቸው ተጠብቆ መግባት እንዲችሉ ዋስትና እሰጣለሁ” ማለቱ መልካም የመጀመሪያ ርምጃ ነው፤ ሆኖም የተፈረመው ስምምነት ባስቸኩዋይ ስራ ላይ ውሎ ለስደተኞቹና ለሌሎቹም ተጎጅዎች አጣዳፊ ርዳታ ይዘን መድረስ እንድንችል ሊደረግ ይገባል ሲሉአሳስበዋል

XS
SM
MD
LG