በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የተመድ የልዑካን ቡድን የጋዛ መተላለፊያን ለመጎብኘት ግብፅ ገብቷል


የተመድ ዋና ፀሓፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ
የተመድ ዋና ፀሓፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ

የተመድ የፀጥታው ም/ቤት የልዑካን ቡድን፣ የጋዛ መተላለፊያ የሆነውን ራፋን ለመጎብኘት ዛሬ ሰኞ ግብፅ ገብቷል። ልዑኩ ግብፅ የገባው ም/ቤቱ በእስራኤል እና በሐማስ መካከል የተኩስ ማቆም ስምምነት እንዲፈፀም ሊያስተላልፍ የነበረውን የውሳኔ ሃሳብ አሜሪካ ድምፅን በድምፅ በሻረች ከቀናት በኋላ ነው።

በግብፅ እና በተባበሩት ዓረብ ኤምሬትስ የተዘጋጀው የአንድ ቀን ጉብኝት በመደረግ ላይ ያለው፣ የሰብዓዊ ቀውሱ እጅግ አሳሳቢ በሆነበት እና የተመድ ዋና ፀሓፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ፣ በጋዛ ያለውን ሁኔታ “የመቃብር ስፍራ” ሲሉ በገለጹበት ወቅት ነው።

የሩሲያን እና የእንግሊዝን ጨምሮ 12 የሚሆኑ አምባሳደሮች የልዑኩ አባላት መሆናቸው ታውቋል።

“በፍልስጤማውያን ላይ እየደረሰ ያለውን ስቃይ እንዳላዩ ማለፍ አይቻልም” ሲሉ የግብፁ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ለልዑካኑ ተናግረዋል።

በተመድ የተባበሩት ዓረብ ኤምሬትስ ልዑክ የሆኑት ላና ኑሰቢህ በበኩላቸው፣ ጉብኝቱ በጋዛ የፍልስጤማውያንን ስቃይ እና ውድመት ብቻ ሳይሆን፣ ተስፋቸውን እና ጥንልካሬያቸውን ለማሳየትም ነው ብለዋል።

የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ መደረስ ባለመቻሉ ቅሬታቸውን የገለጹት በተመድ የፍልስጤማውያን ፍልሰተኞች ድርጅት ኃላፊ ፊሊፔ ላዛሪኒ፣ በጋዛ ሰርጥ ደህንነቱ የተጠበቀ ቦታ እንደሌለ እና አንድ ሚሊዮን ሰዎችን የያዘው የተመድ ሠፈርም ጥቃት እንደደረሰበት አስታውቀዋል።

በጋዛ ረሃብ እንዳለ እና ሰዎች እስከ ሶስት ቀናት ካለምግብ እንደሚያሳልፉ ሓላፊው ጨምረው ገልጸዋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG