በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በሱዳን የተባበሩት መንግሥታት ልዩ ልዑክ ከኃላፊነታቸው ለቀቁ


 ፎቶ ፋይል፦ የተባበሩት መንግሥታት ልዩ ልዑክ ቮልከር ፐርቲስ፣ ካርቱም ሱዳን እአአ ጥር 10/2022
ፎቶ ፋይል፦ የተባበሩት መንግሥታት ልዩ ልዑክ ቮልከር ፐርቲስ፣ ካርቱም ሱዳን እአአ ጥር 10/2022

በሱዳን ወታደራዊ መንግሥት ተቀባይነት ያልነበራቸውና በሀገሪቱ የተባበሩት መንግሥታት ልዩ ልዑክ ቮልከር ፐርቲስ ከሥራቸው መልቀቃቸው ተሰምቷል።

ባለፈው ሰኔ በወታደራዊ መንግሥቱ እንደማይፈለጉና ከሀገር እንዲወጡ የተነገራቸው ልዩ ልዑኩ፣ ከሱዳን ውጪ በመሆን ሥራቸውን ሲያከናውኑ ነበር።

በሱዳን ያለው ግጭት ምንም የመቆም ምልክት እያሳየ እንዳልሆን ቮልከር ፐርቲስ ትናንት ለጸጥታው ምክር ቤት ተናግረዋል።

በሱዳኑ ግጭት ቢያንስ 5ሺሕ ሰዎች እንድሞቱ ሲነገር፣ ቮልከር ፐርቲስ እንደሚሉት ግን ቁጥሩ ዝቅተኛ ግምት ሲሆን፣ ከተጠቀሰውም በላይ ሊሆን ይችላል።

በሱዳን ግጭቱ ከጀመረ በኋላ ቮልከር ፐርቲስ ቁልፍ አደራዳሪ የነበሩ ሲሆን፣ ወታደራዊው መንግሥት ግን በአድሏዊነት ወንጅሉ ወደ ሀግሪቱ መግባት እንደማይችሉ ለተመድ አስታውቆ ነበር።

የሥራ መልቀቂያውን የተቀበሉት የተመድ ዋና ጸሃፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዥ፣ ቮልከር ፐርቲስ “ሥራቸውን ለመልቀቅ በጣም ጠንካራ ምክንያት አላቸው” ብለዋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG