ዋሺንግተን ዲሲ —
“በልዩ ሁኔታ የሚታይ” ወይም “የአስቸኳይ ጊዜ እርምጃ” በሚል ሰበብና ሽፋን ሰብዓዊ መብቶች እንዳይደፈሩ የመንግሥታቱ ድርጅት ከፍተኛ ኮሚሽነር ሚሼል ባሽሌ በአፅንዖት አሳስበዋል።
“የአስቸኳይ ጊዜ ሥልጣናት ሊሠሩ የሚገባቸው ወረርሽኙን በተሳካ ሁኔታ ለመጋፈጥና ለመቆጣጠር ጉዳይ ብቻ ነው ሊሆን የሚገባው፤ አንዲት ነቁጥ ወደፊት፣ አንዲት ነቁጥ ወደኋላ ሊንፏቀቅ ጨርሶ መፈቀድ የለበትም፡፡ መንግሥታት ተቃውሞን እንዲጨፈልቁ፣ ሕዝብን ጨምድደው እንዲቆጣጠሩ፣ ወይም ሥልጣን ላይ ለመቆየት ከጅለው የሚጠቀሙበት መሣርያ ሊሆን ከቶ አይገባም” ብለዋል ኮሚሽነር ባሽሌ።
ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።