ዋሺንግተን ዲሲ —
የተመድ ጠቅላላ ጉባዔና የፀጥታው ጥበቃ ምክር ቤት ትናንት ሐሙስ፣ ለዓለማቀፉ የፍትህ ፍርድ ቤት አራት ዳኞችን መረጠ።
ጠቅላላ ጉባዔውና የፀጥታው ምክር ቤት በተለያዩ ቦታዎች ነገር ግን በተመሳሳይ ሰዓት ባካሄዱት የድምፅ አሰጣጥ፣ የፈረንሳዩን ሩኒ አብርሃምን» የሶማልያውን አንዱልቃዊ አህመድ ዩሱፍን በድጋሚ መርጠዋቸዋል።
ሌሎቹ ሁለቱ አዳዲስ ተመራጮች፣ ከብራዚል አንቶኒዮ ጉተሬዥ አጉስቶ ካንካዶ እና ከሊባኖስ ደግሞ ናዋፍ ሳልማ መሆናቸው ታውቋል።
ሁሉም ከመጪው የካቲት ወር ጀምሮ ለዘጠኝ ወር ነው የተመረጡት።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ