ዋሺንግተን ዲሲ —
የዓለም የጤና ድርጅት በገልፀው መሰረት ሦስቱ ሰራተኞች የተገደሉት ማይ-ማይ የተባለው ተዋጊ ቡድን አማፅያን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የጤና አገልግሎት በሚያንቀሳቅሰው ማዕከል ላይ ዛሬ ማለዳ ጥቃት በከፈቱበት ወቅት ነው። ጥቃቱ የደረሰው በኢቦላ ህክምና የተሰማሩ ሰራተኞች በሚኖሩበት ቢያካቶ የተባለ በኢቱሪ ክፍለ-ሀገር በሚገኝ ከተማ ላይ ነው።
ማንጊና በተባለች ከተማም ሌላ ጥቃት ለማድረስ ተሞክሮ ለመከላከል እንደተቻለ ታውቋል።
የዓለምቀፍ የጤና ድርጅት ኃላፊ ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሐኖም ገብረየሱስ በተፈፀመው ግድያ ማዘናቸውን ገልፀዋል። “እንዲህ ዓይነቱ ሁኔታ እንዳይደርስ የነበረን ስጋት እውን በመሆኑ ልባችን ተሰብሯል” ሲሉ ሃዘናቸውን ገልፀዋል። አሁን ትኩረታችን የቆሰሉትን መንከባከብና በሌሎች አካባቢዎች ያሉትን ሰራተኞች ደህንነት መጠበቃ ላይ ነው ብለዋል።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ