በምሥራቅ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ በኤም 23 አማፂያን እና በኮንጎ የታጠቁ ወታደሮች መካከል ውጊያው እየተባባሰ በመጣበት ወቅት፤ ተፋላሚዎቹ ወገኖች አስገድዶ መድፈርን እና ጾታዊ ጥቃትን እንደ ጦርነት መሳሪያ ጥቅም ላይ እያዋሉት መሆኑን የመንግስታቱ ድርጅት ሰብዓዊ መብት ከፍተኛ ኮሚሽነር ፅህፈት ቤት አስጠንቅቋል።
የመንግስታቱ ድርጅት የሰብዓዊ መብት ጉዳዮች ዋና ሃላፊ ቮልከር ተርክ ቃል አቀባይ የሆኑት ጀርሚ ላውረንስ ሁኔታው “ከግጭት ጋር ተያይዞ ለብዙ አስርት ዓመታት በኮንጎ ታጣቂዎች እየፈጸሙት ያለ ነገር ነው” ብለዋል፡፡
ከፍተኛ ኮሚሽነሩ በተለይም የቅርብ ጊዜው ግጭት “ከግጭት ጋር የተያያዘውን የጾታ ጥቃት የበለጠ ሊያባብሰው ይችላል” ሲሉ አጽንኦት ሰጥተዋል።
በግጭቱ ውስጥ እየተሳተፉ ያሉት የዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ መንግስት፣ የኤም 23 አማፂያን እና ሩዋንዳ በአካባቢው ላለው ቀውስ እርስ በራሳቸው እየተወነንጃጀሉ ነው።
መድረክ / ፎረም