በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ተመድ የሰብዓዊ መብቶች ም/ቤት በሊቢያ ጉዳይ ሪፖርት አወጣ


ፎቶ ፋይል፦ አፍሪካውያን ፍልሰተኞች አነስተኛ የቀን ሥራዎችን ለማግኘት ሊቢያ ዋና ከተማ ትሪፖሊ ድልድይ ስር ሲጠባበቁ።
ፎቶ ፋይል፦ አፍሪካውያን ፍልሰተኞች አነስተኛ የቀን ሥራዎችን ለማግኘት ሊቢያ ዋና ከተማ ትሪፖሊ ድልድይ ስር ሲጠባበቁ።

እአአ ከ2016 ዓ/ም ጀምሮ ሊቢያ ውስጥ ልጆችን በተዋጊነት ማሰለፍን ጨምሮ የጦር ወንጀሎች እና በሰብዕና ላይ የሚፈጸም ወንጀል መድረሱን ተመድ የሰብዓዊ መብቶች ም/ቤት አስታውቋል፡፡

በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት የተቋቋመው ነጻው አጣሪ ቡድን ወደአውሮፓ ለመጓዝ የሚሞክሩ ስደተኞች ሊቢያ ባሉ እስር ቤቶች እና በህገ ወጥ አስተላላፊዎች እጅ ከባድ በደል ይደርስባቸዋል ብሏል።

በስደተኞች ላይ በእስር ቤት ውስጥ የሚደርሱ በደሎች በሰብዓዊነት ላይ የሚደርሱ በመሆናቸው በሊቢያ የጦር ወንጀሎች ተፈጽመዋል ለማለት በቂ ምክንያት አለ ብሏል የተልዕኮው ሪፖርት፡፡

ሪፖርቱ ሕጻናቱን በቀጥታ እጅግ አስከፊ በሆኑ ብጥብጦች እንዲካፈሉ ማድረግ እና ታዋቂ የሆኑ ሴቶችችን የማጥፋት እና መግደል የመሳሰሉ ድርጊቶችም ተዘርዝረውበታል፡፡

XS
SM
MD
LG