በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ተመድ በኢራን ከሂጃብ ጋራ የተያያዙ የመብት ጥሰቶችንና የሞት ቅጣቶችን አወገዘ


ፎቶ ፋይል፦ በቱርክ የምትኖር የኢራን ማኅበረሰብ አባል አንገቷ ላይ "የሞት ቅጣት የለም" ስትል ገመድ ይዛለች።
ፎቶ ፋይል፦ በቱርክ የምትኖር የኢራን ማኅበረሰብ አባል አንገቷ ላይ "የሞት ቅጣት የለም" ስትል ገመድ ይዛለች።

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዐዲስ ባወጣው ዘገባ፣ የኢራን መንግሥት፥ የሂጃብ ሕግን በሚጥሱ ሴቶች ላይ እየፈጸመ ያለውን ከፍተኛ ግድያ እና የኀይል ርምጃ አውግዟል፡፡

ዘገባው እንዳመለከተው፣ እ.ኤ.አ በ2023 ቢያንስ 834 ሰዎች ተገድለዋል። ይህም፣ ከቀደመው ዓመት ጋራ ሲነጻጸር 43 በመቶ ጨምሯል።

ከአደገኛ ዕፆች ጋራ በተያያዙ ወንጀሎች የሚፈጸሙ ግድያዎች፣ በ84 በመቶ ከፍ ማለቱ ሲነገር፣ የአሁኑ በዐሥር ዓመታት ውስጥ ከፍተኛው ነው፤ ተብሏል።

መንግሥታዊ ያልኾነው የኢራን ሰብአዊ መብቶች ድርጅት፣ ባለፈው ዓመት ከአደንዛዥ ዕፅ ጋራ የተዛመዱ 471 ግድያዎችን ዘግቧል፡፡

እስከ አሁን በአውሮፓውያኑ የ2024 ዓመት፣ ቢያንስ 243 የሞት ቅጣቶች መፈጸማቸውን ዘገባው አመልክቷል።

ሂጃብን "በአግባቡ አልተከናነብሽም" በሚል እ.ኤ.አ በመስከረም ወር 2022 የተገደለችውን የማሻ አሚኒን ሞት ተከትሎ ከተካሔደው ተቃውሞ ጋራ በተያያዘ፣ ባለፈው ዓመት ሁለት ሰዎች የሞት ቅጣት ተፈጻሚ ኾኖባቸዋል።

በእነዚኽና በሌሎች የሰብአዊ መብቶች ጥሰት የሚደርሱ ሥቅየቶችንና እንግልቶችን በሚመለከት ተቃውሞዎች ቢሰሙም፣ የኢራን መንግሥት የሂጃብ ሕግን ማስከበሩንና ማጠናከሩን ቀጥሏል።

በተባበሩት መንግሥታት የኢራን አምባሳደር፣ ሪፖርቱን "ከፖለቲካ ጋራ የተያያዘ ነው፤" በማለት ተችተው፣ የሞት ቅጣት እንዲቋረጥ የቀረበላቸውን ጥሪ ውድቅ አድርገዋል።

አምባሳደሩ፣ የሞት ቅጣትን ለከባድ ወንጀሎች የመጠቀሙን አግባብነት ለማስጠበቅ በመሟገት፣ ለኢራን የዴሞክራሲ ቁርጠኝነት አጽንዖት ሰጥተዋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG