በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ተመድ በሱዳን ተቃዋሚዎች ደርሷል የተባለው የጾታ ጥቃት እንዲጣራ ጠየቀ


በካርቱም የተደረገው ሰላማዊ ሰልፍ
በካርቱም የተደረገው ሰላማዊ ሰልፍ

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ባለሥልጣናት የሱዳን ባለሥልጣናት ባለፈው እሁድ በካርቱም በተደረገው ሰላማዊ ሰልፍ ላይ ተሳታፊ የነበሩ በርካታ ሴቶችና ልጃገረዶችን አስገድዶ ደፍረዋል በተባሉት የጸጥታ ኃይሎች ላይ ምርመራ እንዲያካሂዱ ጥሪ አድርገዋል፡፡

የድርጅቱ ቃል አቀባይ ሊዝ ትሮሴል ሰላማዊ ሆኖ የተጀመረው ተቃውሞ ሁከት የተሞላበትና የጸጥታ ኃይሎች ወደ ፈጸሙት ድብደባና አስገድዶ መድፈር የተቀየረው ወዲያኑ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ቃል አቀባዩ በሱዳን የሚገኙ ተወካዮቻቸው በግርግሩ ወቅት ሰልፉ ላይ የነበሩ 13 ሴቶችና ልጃገረዶች በቡድን መደፈራቸውን ሪፖርት የደረሳቸው መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ስለደረሳቸው ሪፖርት ሲያስረዱም “በሰልፉ ላይ ከተነሳ ግርግርና ሁከት አምልጠው እሁድ ማታ በቤተመንግሥቱ አካባቢ የነበሩ ሴቶች ላይ አስገድዶ መድፈር የተፈጸመባቸው መሆኑን መረጃው ደርሶናል፡፡ ሁለት ሰልፈኞችም በተተኮሰባቸው ጥይት ህይወታቸው አልፏል ሶስት መቶ የሚሆኑን ደግሞ ቆስለዋል አንዳንዶቹ በጥይት የተመቱ ሲሆን አንዳንዶቹ በአስለቃሽ ጋዝ ሌሎች ደግሞ በጸጥታ ኃይሎች ድብደባ ተፈጽሞባቸዋል ብለዋል፡፡

ሱዳናውያን በሱዳን የተደረገው ወታደራዊ ግልበጣ መቃወማቸውን የቀጠሉ ሲሆን እኤአ 2019 ላይ ለፕሬዚዳንት ኦማር አልበሽር መንግሥት መገልበጥ ምክንያት የሆነውን ህዝባዊ አመጽ ሦስተኛ ዓመት ምክንያት በማድረግም ባለፈው እሁድ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ሰልፈኞች ተቃውሞቸውን ማሰማታቸው ይታወቃል፡፡

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰአብአዊ መብት ኮሚሽን የሱዳን ባለሥልጣናት ተፈጽሟል የተባለውን የሰብአዊ መብት ጥሰት የሚያጣሩ ኮሚቴ እንዲያቋቁሙና ጥፋተኞ ሆነው የተገኙት ተጠያቂ እንዲሆኑን አሳስበዋል፡፡

XS
SM
MD
LG