በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ተመድ በሊቢያ የፍልሰተኞችን ግድያ አወገዘ


ፎቶ ፋይል፦ ፍልሰተኞችን አሳፍራ በባህር ወደ አውሮፓ ስትጓዝ የነበረች መርከብ ሰምጣ ፍለሰተኞች መሞታቸው ተከትሎ የሊቢያ የጤና ባለሙያዎች እና የሊቢያ ቀይ ጨረቃ ማኅበር ሰራተኞች አስከሬኖችን ከባህር እያወጡ፣ ከሊቢያ ዋና ከተማ ትሪፖሊ በምዕራብ 120 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው ሳብራታ ባህር ዳርቻ ላይ እአአ 11/25/2021
ፎቶ ፋይል፦ ፍልሰተኞችን አሳፍራ በባህር ወደ አውሮፓ ስትጓዝ የነበረች መርከብ ሰምጣ ፍለሰተኞች መሞታቸው ተከትሎ የሊቢያ የጤና ባለሙያዎች እና የሊቢያ ቀይ ጨረቃ ማኅበር ሰራተኞች አስከሬኖችን ከባህር እያወጡ፣ ከሊቢያ ዋና ከተማ ትሪፖሊ በምዕራብ 120 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው ሳብራታ ባህር ዳርቻ ላይ እአአ 11/25/2021

በሜዲትሬንያን ጠርፍ ላይ በምትገኘው ሳብራታ በተሰኘች የሊቢያ ከተማ ውስጥ 15 ፍለሰተኞች መገደላቸውን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ትናንት አውግዞ፣ ለድርጊቱ ህገወጥ ሰው አስተላላፊዎችን ወንጅሎ ለፍርድ እንዲቀርቡ ጠይቋል።

አስከሬኖቹ በባህር ዳርቻው ላይ ተንሳፈው የተገኙ ሲሆን፣ አብዛኞቹ ጀልባ ውስጥ ተቃጥለው የከሰሉ መሆናቸውን ተመድና የሊቢያ ቀይ ጨረቃ ማኅበር አስታውቀዋል ሲል የፈረንሳይ ዜና ወኪል ኤኤፍፒ ዘግቧል።

በሊቢያ የተመድ ልዑክ እንዳለው፣ የአሟሟታቸው ትክክለኛ ምክንያት ወደፊት የሚወሰን ቢሆንም፣ ግድያው የተፈጸመው በተቀናቃኝ አስተላላፊዎች መካከል የተፈጠረን ግጭት ተከትሎ እንደነበር ሪፖርቶች ይጠቁማሉ።

“አፋጣኝ፣ ገለልተኛ እና ግልጽ ምርመራ አድርገው ድርጊቱን የፈጸሙትን ለፍርድ እንዲያቀርቡ” ሲል የተመድ የሊቢያ ባለሥልጣናትን ጠይቋል።

ሞአመር ጋዳፊ ከ11 ዓመት በፊት ከሥልጣን ከመወገዳቸውም በፊት ቢሆን፣ ሊቢያ የህገወጥ አስተላላፊዎች መስመር ነበረች። ከጋዳፊ በኋላ ሃገሪቱ ወደ አውሮፓ ለሚሄዱ ፍልሰተኞች በዓለም እጅግ አደገኛው መንገድ ነው ተብሏል።

ፍልሰተኞች አብዛኛውን ግዜ በአስተላላፊዎቻቸው ሰቆቃ ይደርስባቸዋል።

ባለሥልጣናትና ታጣቂ ቡድኖች በፍልሰተኞቹ ላይ ስቃይና ሌሎች በደሎች በመንግሥት እውቅና ይፈጽማሉ ሲሉ የሰብዓዊ ቡድኖች ይከሳሉ።

የሊቢያ መገናኛ ብዙሃን እንደዘገቡት፣ በአስተላላፊ ቡድኖች መካከል ጭቅጭቅ ከተነሳ በኋላ፣ በአብዛኛው ከደቡባዊ አፍሪካ በመጡት ፍልሰተኞች ላይ የጥይት እሩምታ አርከፍክፈውባቸዋል። ሪፖርቶቹ ጭምረው እንዳሉት አንደኛው ቡድን ጀልባዋ ላይ እሳት ለቆባታል።

በያዝነው የፈረንጆች ዓመት ብቻ፣ 14ሺህ ፍልሰተኞች ተይዘው ወደ ሊቢያ መመለሳቸውን ዓለም አቀፍ የፍልሰተኞች ድርጅት ዛሬ አስታውቋል።

ሜዲትሬኒያን ባህርን ለመሻገር ሲሞክሩ ቢያንስ 216 ፍልሰተኖች ሲሞቱ፣ 724 ደግሞ የደረሱበት ባይታወትቅም፣ ሳይሞቱ እንዳልቀረ ይታመናል።

XS
SM
MD
LG