ዋሺንግተን ዲሲ —
ጋዛ ውስጥ በእሥራኤልና በፍልሥጤማውያን መካከል ግጭት ሲደርስ ከ5 ዓመታት ወዲህ የከፋው ነው ያለውን ሁኔታ አስመልክቶ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት ዛሬ አስቸኳይ ስብሰባ ለማድረግ ተዘጋጅቷል።
በዓለሙ ድርጅት የመካከለኛው ምሥራቅ የሰላም ሂደት ልዩ አስተባባሪ ኒኮላይ መላዴኖቨ ስለ ወቅቱ ሁኔታ ከእየሩሳሌም ሆነው ለምክር ቤቱ ማብራሪያ ይሰጣሉ ተብሎ እየተጠበቀ ነው።
በእሥራኤል ኃይሎች የተገደሉትን በደርዘኖች የተቆጠሩ ፍልሥጤማውያን አስመልክቶ የቀረበውን የውግዘትና ሐዘን መግለጫ ያረቀቀችው ኩዌት በገለልተኛ አካል እንዲጣራም ጥሪ አቅርባለች።
የእሥራኤል ሸሪክ የሆነችው ዩናይትድ ስቴትስ ድምፅን በድምፅ የመሻር ሥልጣኗን ተጠቅማ - ረቂቁ እንዳያልፍ አሳግዳለች።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ