በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የዓለም አየር ግለትን የሚገድቡ ጠንካራ እርምጃዎች እንዲወሰዱ ጥሪ ቀረበ


ሀገሮች የአየር ንብረት ጉባኤ ላይ ድርድር እየተደረገበት ባለው ረቂቅ ሰነድ ግላስጎ ስኮትላንድ ውይይት እያደረጉ ነው
ሀገሮች የአየር ንብረት ጉባኤ ላይ ድርድር እየተደረገበት ባለው ረቂቅ ሰነድ ግላስጎ ስኮትላንድ ውይይት እያደረጉ ነው

ግላስጎ ስኮትላንድ ላይ ድርድር የተካሄደ ባለው የአየር ንብረት ጉባኤ ላይ ድርድር እየተደረገበት ባለው ረቂቅ ሰነድ ሀገሮች የካርቦን ልቀታቸውን ለመቀነስ የሚያደርጉትን ጥረት በአስቸኳይ ማጠናከር እንደሚገባቸው ያሳስባል።

የዓለም አየር ግለትን ለመቆጣጠር የሚቻለው ያን ካደረጉ መሆኑን የሚያሳስበው እና ዛሬ ይፋ የሆነው ሰነድ እአአ ለ2030 የተወጠነውን ግብ ለማሳካት ያላቸውን ዕቅድ እንደገና እንዲገመገሙት ይጠይቃል።

የበለጸጉት ሃገሮች ደሆች ሃገሮችን በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት የሚገጥማቸውን ችግሮች መወጣት እንዲችሉ ሊረዱ የሚገባ መሆኑንም ያሳስባል።

በአየርን ንብረት ጉባኤው ላይ እየተካፈሉ ያሉት ቁጥራቸው ወደ 200 የሚጠጉ ሃገሮች በቀረበው ሰነድ ላይ የሚያደርጉት ድርድር በርካታ ቀናት እንደሚወስድ ይጠበቃል።

XS
SM
MD
LG