በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የዓለምን ሙቀት መጨመር ማቆም በማይችልበት ደረጃ ላይ ደርሷል


ፎቶ ፋይል፦ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የአየር ንብረት ለውጥ ሪፖርት የዓለም ሙቀት በአደገኛ ሁኔታ እየጨመረ መምጣቱንና ሊቀለበስ በማይችልበት ደረጃ ላይ መድረሱን ገልጿል።
ፎቶ ፋይል፦ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የአየር ንብረት ለውጥ ሪፖርት የዓለም ሙቀት በአደገኛ ሁኔታ እየጨመረ መምጣቱንና ሊቀለበስ በማይችልበት ደረጃ ላይ መድረሱን ገልጿል።

የዓለም ሙቀት በአደገኛ ሁኔታ እየጨመረ መምጣቱንና ሊቀለበስ በማይችልበት ደረጃ ላይ መድረሱን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አስታውቋል። ሆኖም ሊደርስ የሚችለውን የከፋ አደጋ ለመከላከል ግን ርምጃዎችን መውሰድ እንደሚቻል ድርጅቱ ጨምሮ ገልጿል። ድርጅቱ ሰኞ እለት ይፋ ያደረገው ሪፖርት አስመልክቶ የአሜሪካ ድምፅ ያጠናከረውን ዘገባ ነው።

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በአየር ንብረት ለውጥ ዙሪያ በመንግሥታት መሃከል የሚያካሂደው የውይይት መድረክ ትላንት በስዊዘርላንድ ባወጣው መግለጫ የአየር ንብረት ለውጥ እየደረሰ ያለው - የሰው ልጆች በ 19ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ከነበረው የኢንዱስትሪ ዘመን በፊት አንስቶ ሲያደርጓቸው የነበሩት እንቅስቃሴዎች መሬት ከ1.1 ዲግሪ ሴልሽየስ በላይ እንዲሞቅ በማድረጉ መሆኑ የማያጠራጥር ነው - ሲል አስታውቋል።

የውይይት መድረኩ ሊቀመንበር የሆኑት ሆውሳንግሊ እንደተናገሩት የአየር ንብረት ለውጥ በመላው አለም ላይ የሚገኙ ሰዎችን ህይወት በሙሉ ህይወት የሚያቃውስ ነው።

"በመጀመሪያ ደረጃ የሰዎች እንቅስቃሴ የአየር ንብረት መዛባትን እያስከተለ ለመሆኑ ምንም ክርክር አያስፈልገውም። በሁለተኛ ድረጃ የአየር ንብረት ለውጥ ተፅእኖ እያደረሰ ያለው በፕላኔታችን ላይ የሚገኘውን ሁሉንም አገራት ነው። በመጨረሻ ደግሞየዓለም ሙቀትን ለመቀነስ ጠንካራ፣ ፈጣንና ዘላቂነት ባለው መልኩ የካርበንዳይኦክሳይድ እና ሌሎች በካይ ጋዞችን ልቀት መቀነስ ያስፈልጋል።"

የአየር ንብረት ለውጥ ሁኔታ ላይ የሚወያየው የመንግስታቱ ጥምረት እንዳስጠነቀቀው የዓለማችን ሙቀት እንደ ገደብ ከተቀመጠው የ1.5 ዲግሪ ሴልሺየስ የሙቀት መጠን ሊደርስ ወይም ሊያልፍ ይችላል። ይሄ ደግሞ ግግር በረዶዎች እንዲቀልቱ፣ የባህር ወለል መጠን እንዲጨምርና አውዳሚ የጎርፍ አደጋዎችና ድርቆች እንዲከሰቱ ያደርጋል።

ሆኖምለካርበን ዳይ ኦክሳይድ ልቀት ከፍተኛ አስተዋፅኦ የሚያደርገውንና በከባቢ አየር ላይ ጉዳት የሚያስከትለውን የፎሲል ነዳጅ ምርቶችን በአስቸኳይ መጠቀም በማቆም በዓለም ዙሪያ የሚደርሰውን ጉዳት መቀነስ ይቻላል ሲል 195 አባል ሀገራት ያፀደቁት የመንግስታቱ ድርጅቱ ሪፖርት ጠቁሟል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

የዓለምን ሙቀት መጨመር ማቆም በማይችልበት ደረጃ ላይ ደርሷል
please wait

No media source currently available

0:00 0:02:30 0:00


XS
SM
MD
LG