ዋሽንግተን ዲሲ —
በሶማልያ ከፍተኛው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዲፕሎማት ትላንት ሲናገሩ፥ ሶማልያ ጨነገፉ ከሚባሉት ሀገሮች ተርታ ወጥታ ወደ ማገገም ባደረገችው የለውጥ ጉዞ በደንብ ተራምዳለች ብለዋል።
መንግስታቱን ድርጅት ወክሎ በሃገሪቱ የሚገኘው ኒኮላ ኬይ (Nicholas Kay) እአአ 2016ዓ. ም. ለሶማልያ በበርካታ ግንባሮች ወሳኝ ይሆናል ሲሉ ለፀጥታው ምክር ቤት አስረድተዋል።
የቪኦኤዋ ማርገሬት ባሽር እና መጋን ዱዞር (Margaret Besheer and Megan Duzor) ዝርዝሩን ልከዋል፣ ሰሎሞን ክፍሌ አቅርቦታል። ይህንን ፋይል ያዳምጡ።