በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ቻይናና ሩሲያ በሰሜን ኮሪያ የኢኮኖሚ ማዕቀብ እንዲነሳ የጸጥታው ም/ቤትን አሳሰቡ


የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የፀጥታ ጥበቃ ምክር ቤት አርማ
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የፀጥታ ጥበቃ ምክር ቤት አርማ

ቻይና እና ሩሲያ፣ ሰሜን ኮሪያ ላይ የተጣለው የኢኮኖሚ ማዕቀብ እንዲያበቃ የሚጠይቅ የጋራ መግለጫ በማውጣት ለተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የጸጥታ ምክር ቤት ለማቅረብ እየተዘጋጁ ነው፡፡

በኢኮኖሚው ማዕቀብ እንዲነሱ ከሚጠይቋቸው ነገሮች ውስጥ፣ በውጭ አገር የሚሰሩ የሰሜን ኮሪያ ሠራተኞች ወደ አገራቸው ገንዘብ መላክ እንዲችሉ፣ ሰሜን ኮሪያ የባህር ምግቦችን፣ ጨርቃጨቅ ምርቶችን፣ ወደ ወጭ መላክ ማድረግ እንድትችል፣ እንዲሁም ወደ አገር ውስጥ በሚገባው የነዳጅ ምርት ላይ የተጣለው ማዕቀብ እንዲያበቃ የሚጠይቅ ነው፡፡

በአሶሼይትድ ፕሬስና በሮይተርስ በተናጥል የተገኙት የመግለጫዎቹ ረቂቅ የውሳኔ ሀሳቦች በሰሜን ኮሪያ “የሰላማዊ ዜጎችን ህይወትና አኗኗር ለማጠንከር በማሰብ” በሚል አስራ አምስቱን የጸጥታ ምክርቤት አባላት ለማሳሰብ የተዘጋጀ መሆኑን ተመልክቷል፡፡

የተባበሩት መንግሥታት፣ በኒዩክለየርና ባለስቲክ ሚሳዬል መሳሪያዎች ፕሮግራሟ የተነሳ፣ በሰሜን ኮሪያ ላይ የመጀመሪያውን ማዕቀብ የጣለው እኤአ 2006 ነው፡፡

ይሁን እንጂ ሰሜን ኮሪያ የምጣኔ ሀብቷ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተዳከመ ቢሄድም፣ የባለስቲክና የሚሳዬል መሳሪያዎች ሙከራ ግን ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረና እየተጠናከረ መሄዱ በዘገባው ተመልክቷል፡፡

የውሳኔ ሀሳቡ በቻይናና ሩሲያ እየተስፋፋ የመጣው፣ እኤአ በ2019 ቢሆንም፣ በዩናይትድ ስቴትስ እና በሌሎች ምዕራባዊያን አገሮች ተቃውሞ ለምክር ቤቱ ሳይቀርብ ቀርቷል፡፡

XS
SM
MD
LG