በዓለም ላይ እየተካሄዱ ባሉ የትጥቅ ግጭቶች በሕፃናት ላይ ተደርሱት ጥቃቶች እየጨመሩ መሆናቸውን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አስታውቋል።
ከእስራኤል እስከ የፍልስጤማውያን ግዛቶች፤ ከሱዳን እስከ ሚያንማር እና ዩክሬን ባለፈው 2023 በነበሩ የትጥቅ ግጭቶች በሕፃናት ላይ የሚደርሱ ጥቃቶች በከፍተኛ መጠን መጨመራቸውን፣ በግጭት አካባቢዎች የሚገኙ ሕፃናትን ሁኔታ የሚያሳየው ዓመታዊ ጥናት አመልክቷል።
ጥቃቱ በ21 በመቶ መጨመሩን፤ በኮንጎ፣ ቡርኪና ፋሶ፣ ሶማሊያ እና ሶሪያ ያለውን ሁኔታ የዳሰሰው ጥናት አመልክቷል። ጥናቱ ከ18 ዓመት በታች የሆኑትን የሚመለከት ነው።
በተመድ የሚካሄደው ዓመታዊ ጥናት እስራኤልን ለመጀምሪያ ጊዜ በሕፃናት ላይ ጥቃት በመሰንዘር የሚጠየቁ ሃገራት ዝርዝር ውስጥ አካቷል። ሐማስ በሰነዘረው ጥቃትና እስራኤል በሰጠቸው የአጸፋ ምላሽ ምክንያት በሕፃናት ላይ የደረሰው ከፍተኛ ጥቃት በ155 በመቶ እንዳሻቀበ ጥናቱ ጠቁሟል።
መድረክ / ፎረም