ፍልሚይ ላይ ያሉት ሁለቱ የሱዳን ተቀናቃኝ ጄኔራሎች ባስቸኳይ ውጊያውን እንዲያቆሙ የተመድ ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዥ ጥሪ አቀረቡ፡፡ ውጊያው ወደተራዘመ ጦርነት እንዳይቀየር ሲሉም አስጠነቀቁ፡፡
ዋና ጸሐፊ ጉቴሬዥ ትናንት ማክሰኞ ማታ በሱዳን ጉዳይ ላይ ለተሰበሰበው የጸጥታ ምክር ቤቱ ስብሰባ ባደረጉት ንግግር
“ግጭቱ የሚፈታው ውጊያ ሜዳ ላይ በሚወድቀው የሰላማዊ ሰዎች አስከሬን አይደለም ሊሆንም አይገባም” ብለዋል፡፡
ተፋላሚዎቹ ወገኖች በዩናይትድ ስቴትስ ሽምግልና ሰኞ ዐኩለ ሌሊት ላይ ስራ ላይ የዋለውን የየ72 ሰዐት ተኩስ አቁም ማክበር እንዳለባቸው ዋና ጸሐፊው አሳስበዋል፡፡
በጄኔራል አብደልፋታህ አል ቡርሃን የሚመሩት የሀገሪቱ የጦር ኅይሎች እና በጄኔራል መሐመድ ሀምዳን ዳጋሎ የሚመሩት ፈጥኖ ደራሽ ኃይሎች ተኩስ አቁሙን እንደሚያከብሩ ቃል ገብተዋል፡፡ ከብዙ መቶ የድርጅቱ ሰራተኞች ጋር ካርቱምን ለቅቀው ፖርት ሱዳን የሚገኙት የመንግሥታቱ ድርጅት ከፍተኛው የሱዳን ዲፕሎማት ቮልከር ፐርቲዝ ለጸጥታ ምክር ቤቱ ስብሰባ በቪዲዮ አማካይነት ባደረጉት ገለጻ የተኩስ አቁም ስምምነቱ ሥራ ላይ የዋለው በተወሰኑ የሀገሪቱ አካባቢዎች ብቻ መሆኑን አመልክተዋል፡፡ ሁለቱም ወገኖች አንዱ ሌላው ተኩስ አቁሙን በመጣስ እየተወነጃጀሉ መሆናቸውንም አክለው ገልጸዋል፡፡
ውጊያው መቀጠሉን የወታደሮች እንቅስቃሴም እንዳለ እየሰማን ነው” ያሉት የተመዱ የሱዳን ከፍተኛው ዲፕሎማት ካርቱም ውስጥ በሪፐብሊካን ቤተ መንግሥት በዐለም አቀፉ የአውሮፕላን ማረፊያ በጦር ኅይሎች ዋና መሥሪያ ቤት እና በፈጥኖ ደራሽ ሃይሉ ካምፖች ውጊያ መኖሩን ከበፊቱ የባሰ ከባድ ውጊያ የሚካሄድባቸው አካባቢዎች እንዳሉም ሰምተናል”
“ውጊያው መቀጠሉን የወታደሮች እንቅስቃሴም እንዳለ እየሰማን ነው” ያሉት የተመዱ የሱዳን ከፍተኛው ዲፕሎማት ካርቱም ውስጥ በሪፐብሊካን ቤተ መንግሥት በዐለም አቀፉ የአውሮፕላን ማረፊያ በጦር ኅይሎች ዋና መሥሪያ ቤት እና በፈጥኖ ደራሽ ሃይሉ ካምፖች ውጊያ መኖሩን ከበፊቱ የባሰ ከባድ ውጊያ የሚካሄድባቸው አካባቢዎች እንዳሉም ሰምተናል” ብለዋል፡፡
“በተለይ ባሂሪ እና ኡምዱርማን ከተሞች ውስጥ የአየር እና የከባድ መሳሪያ ድብደባው መቀጠሉ ተነግሮናል” ሲሉም የዐለሙ ድርጅት ዲፕሎማት አመልክተዋል፡፡ ኡምዱርማን 2 ነጥብ 3 ሚሊዮን ህዝብ የሚኖርባት ሁለተኛዋ የሱዳን ትልቋ ከተማ ነች፡፡
አክለውም ዳርፉር ውስጥም በምዕራቡና ደቡቡ አካባቢ ውጊያው መቀጠሉን የገለጹት ቮልከት ፐርቲዝ በምዕራብ ዳርፉር ያሉ ጎሳዎች አባላት ውጊያውን ሊቀላቀሉ እየታጠቁ ነው የሚሉ ሪፖርቶች እንዳሳሰቧቸው አስታውቀዋል፡፡
“በውጊያው ጎራ ለይተው ለመዋጋት እየተንቀሳቀሱ ያሉ የጎሳ አባላት መኖራቸውን የሚጠቁሙ ሪፖርቶች አሉ፡፡ ይህ አጎራባች ሀገሮችን ውጊያው ውስጥ እንዲገቡበት ሊያደርግ ስለሚችል አደገኛ ነው” ብለዋል፡፡
በውጊያው እስካሁን ቢያንስ 427 መገደላቸውን እና ወደ 4000 የሚደርሱ ሌሎች ሰዎች መቁሰላቸውን የገለጡት ቮልከር ፐርቲዝ ቁጥሩ እየጨመረ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ከተገደሉት መካከል አራቱ የዕርዳታ ሰራተኞች ሲሆኑ አንድ የግብጽ ዲፕሎማትም ተገድለዋል፡ ተዋጊዎቹ ወገኖች ሲቪሎች ውጊያ ከሚካሄድባቸው አካባቢዎች ጥቃት ሳይደርስባቸው መውጣት እንዲችሉ ያደርጉ ዘንድ የተ መ ዱ የሱዳን ዋና ዲፕሎማት ጥሪ አቅርበዋል፡፡