ዋሺንግተን ዲሲ —
የተመድ ዋና ጸሃፊ ኮንጎ ዲሞክራሲያዊት ሪፖብሊክ ውስጥ በድርጅቱ ሰላም አስከባሪዎች ላይ የተፈፀምው ጥቃት እንዳስቆጣቸው ገለፁ ።
ምሥራቅ ኮንጎ ውስጥ ብዛት ያላቸው ታንዛናውያን ሰላም አስከባሪዎች መገደላቸውን ተከትሎ ዋና ጸሃፊው አንቶንዮ ጉተሬዝ ባወጡት መግለጫ ይህ ሆን ተብሎ የተፈፀመ ጥቃት ከጦርነት ወንጀል የሚቆጠር ነው ብለዋል።
በጥቃቱ ከአርባ የሚበልጡ ሰላም አስከባሪዎች ቆስዋል።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ