በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ጉተሬዥ በዩክሬን የተከማቸውን እህል ወደ ውጭ ለመላክ አጠቃላይ ስምምነት መኖሩን ተናገሩ


የተባበሩት መንግሥታት ዋና ጸሀፊ አንቶኒዮ ጉተሬዥ
የተባበሩት መንግሥታት ዋና ጸሀፊ አንቶኒዮ ጉተሬዥ

የተባበሩት መንግሥታት ዋና ጸሀፊ አንቶኒዮ ጉተሬዥ በዩክሬን የተከማቸውን እህል ወደ ውጭ ለመላክ አጠቃላይ ስምምነት መኖሩን ተናገሩ፡፡

ጉተሬዥ፣ ሩሲያ ዩክሬንን ከወረረችበት እኤአ የካቲት 24 አንስቶ፣ በዩክሬን የተከማቸውን በሚሊዮኖች ቶኖች የሚቆጠር እህል ኤክስፖርት ለማድረግ፣ በሩሲያና በዩክሬን መካከል በሚደረገው ስምምነት፣ በሩሲያ እና በዩክሬን፣ እንዲሁም በቱርክና በተባበሩት መንግሥታት መካከል “አጠቃላይ ስምምነት” መኖሩን አስታውቀዋል፡፡

“የዛሬው አስፈላጊና ውጤታማ እርምጃ ነው” ሲሉ በአራቱ ወገኖች በኢንስታንቡል እየተደረገ ያለው ንግግር ስለሚገኝበት ሁኔታ፣ ትናንት ረቡዕ ለሪፖተሮች በሰጡት መግለጫ የተናገሩት ጉተሬዥ “ወደ ተሟላው ስምምነት የሚወስድ አንድ እምርጃ ነው” ብለዋል፡፡

ከሩሲያ ዩክሬንና የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጋር የማስተባበር ማዕከልን መፍጠርን፣ እህሎቹ የሚተላለፉባቸውን ወደቦችን መቆጣጠርንና ከኦዴሳ እህል ጭነው የሚወጡ መርከቦችን ደህንነት መጠበቅን ጨምሮ፣ በዋና ዋና ጉዳዮች ላይ ስምምነት አለ በማለት የቱርክ የመከላከያ ሚኒስትር፣ በሰጡት መግለጫ ላይ በይፋ አስተያየት ሳይሰጡ የቆዩት የተባበሩት መንግሥታት ዋና ጸሀፊ ዝምታቸውን ሰብረዋል፡፡

“አዎ በርግጥ ይህ የመጀመሪያው ስብሰባ ነው” ያሉት ጉተሬዥ” የታየው መሻሻል እጅግ የሚበረታታ ነበር፡፡ አሁን ልኡካኑ ወደ የአገራቸው ዋና ከተማ ተመልሰዋል፣ የሚቀጥለው ሂደት ይፋ ወደ ሆነው መደበኛ ስምምነት ያደርሰናል ብለን ተስፋ እንዳደርጋለን” ብለዋል፡፡

ምንም እንኳ ጉተሬዥከመጨረሻው ስምምነት የሚደረሰበት ቀን መች እንደሆነ ባይተነብዩም፣ ተሳታፊዎቹ ወገኖች በሚቀጥለው ሳምንት ተገናኝተው ከመጨረሻው ስምምነት ይደርሳሉ ብለው ተስፋ እንደሚያደርጉ ተናግረዋል፡፡

በየትኛውም ቀን ቢሆን ወደ ኢስታንቡል በመሄድ ስምምነቱን ለመፈረም ዝግጁ መሆናቸውንም ዋና ጸሀፊው አመልክተዋል፡፡

XS
SM
MD
LG