በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሰላም መንገድ ለሴንትር አፍሪክ


ፕሬዚዳንት ፎስቲን አርሻንዥ ቱዴራ
ፕሬዚዳንት ፎስቲን አርሻንዥ ቱዴራ

በጦርነትና ብጥብጥ ለተዋጠችው ማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ ወደ ሰላም መሄጃው መንገድ አጥፍቶ አለመቀጣትን መዋጋት መሆኑን የማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት አስታወቁ።

በጦርነትና ብጥብጥ ለተዋጠችው ማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ ወደ ሰላም መሄጃው መንገድ አጥፍቶ አለመቀጣትን መዋጋት መሆኑን የማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት አስታወቁ።

ፕሬዚዳንት ፎስቲን አርሻንዥ ቱዴራ ለተባበሩት መንግሥታት የሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት ባደረጉት ንግግር የሰላማቸው አቅጣጫ ሰዎች ለፈፀሙት አድራጎት ተጠያቂ እንዲሆኑ ማድረግ እንደሆነ ተናግረዋል።

የሴንትር አፍሪክ ቀውስ በአውሮፓ የዘመን አቆጣጠር በ2013 ዓ.ም የተቀጣጠለው በአብዛኛቸው ሙስሊም የሆኑ ‘ሴሌካ’ አማፂያን ዋና ከተማዪቱን ባንጊን ይዘው ሥልጣን ሲቆጣጠሩና አብላጫቸው ክርስትያን የሆኑት ‘አንታይ ባላካ’ የሚባሉት ነፍጥ አንጋቾች የአፀፋ ጥቃት ማድረስ ሲጀምሩ ነበር።

በሃገራቸው ውስጥ እጅግ የተንሠራፋው የሰብዓዊ መብቶች ሁኔታ የመንግሥቱን ሥልጣን እጅግ ማዳከሙንና የፍርዱን ሥርዓት ነፃነትም አብዝቶ መጋፋቱን ፕሬዚዳንት ቱአዴራ ለሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤቱ አመልክተዋል።

“በሰላምና በፍትሕ መካከል አንዳችም ተቃርኖ የለም” ያሉት ፕሬዚዳንት ቱአዴራ የወንጀሎች ሰለባዎችና ተጎጂዎች ፍትህ ሊያገኙና ሊካሱም እንደሚገባ ተናግረዋል።

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

የሰላም መንገድ ለሴንትር አፍሪክ
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:06 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG