በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የተመድ በጦርነት የተጠመዱ ህፃናት ዓመታዊ ሪፖርት


የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የየመን ሁቲ አማጽያንን የሚወጋውን በሳውዲ አረቢያ የሚመራ ጥምረት ለሁለት ተከታታይ ዓመት ህፃናትን የሚገድሉ ኃይሎች መዘገቡ ውስጥ ከትቶታል።

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የየመን ሁቲ አማጽያንን የሚወጋውን በሳውዲ አረቢያ የሚመራ ጥምረት ለሁለት ተከታታይ ዓመት ህፃናትን የሚገድሉ ኃይሎች መዘገቡ ውስጥ ከትቶታል።

መዝገቡ በመንግሥታቱ ድርጅት በጦርነት የተጠመዱ ህፃናት ዓመታዊ ሪፖርት ተካትቶ ትናንት ለፀጥታው ምክር ቤት ተሰጥቷል።

ሪፖርቱ ሳውዲ መራሹ ጥምረት ባለፈው እኤአ 2016 ስድስት መቶ ሰማኒያ ሦስት የየመን ህፃንትን ገድሏል ወይም አቁስሏል፣ በትምህርት ቤቶችና ሆስፒታሎች ላይ ሠላሳ ሥምንት ጥቃቶችን አድርሷል ብለዋል።

በኢራን የሚደገፉት ሁቲ አማፅያን የየመን አልቃይዳ ጨምሮ የመን ውስጥ የሚዋጉት ሌሎቹ ክፍሎች ደግሞ ህፃናትን ከጦርነት መከራ ሳይጠብቁ ቀርተዋል ተብለው በሌላ መዝገብ ላይ ተፈርጀዋል።

ሳውዲ በውጊያው ህጻናት እንዳይጎዱ ዕርምጃዎች እየወሰድን ነን ብትልም ልጆቹ የሚገደሉበትንና የሚቆስሉበትን ተጨባጭ ሁኔታ ያስከተለው በርሷ የሚመራው ጥምረት አድራጎት መሆኑን ሪፖርቱ አስረድቷል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG