በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሊቢያ መንግሥት ከጄኔቫ የሰላም ድርድር ወጣ


ዓለምቀፉ ማኅበረሰብ ዕውቅና የሰጠው የሊቢያ መንግሥት ጄኔቫ ላይ በተመድ አመቻችነት እየተካሄደ ካለው የሰላም ድርድር ወጣ።

የትሪፖሊው መንግሥት ዛሬ ይህን ርምጃ የወሰደው የተቀናቃኙ መንግሥት ኃይሎች ትሪፖሊ ወደብን ከደበደቡ በኋላ መሆኑ ተገልጿል። ጥቃቱ ከባድ የአካባቢ ደኅንነት አደጋ ሊያስነሳ ነበር ተብሏል።

የቀድሞው ጄኔራል ሃሊፋ ሃፍታር የሊቢያ ብሄራዊ የጦር ሰራዊት ወደቡን በሚሳይል የደበደበ ሲሆን በስፍራው የነበረ የነዳጅ ዘይት ማጓጓዣ በጥቂት ሜትር ርቀት እንደሳተው የተገለጸ ሲሆን ቢመታው ኖሮ ከባድ የተፈጥሮ አካባቢና ሰብዓዊ ጥፋት ያደርስ ነበር ሲሉ የመንግሥቱ የነዳጅ ኮርፖሬሽን ሃላፊ አመልክተዋል።

የሃፍታር ኃይሎች መጀመሪያ ዒላማ ያደረግነው ለመንግሥት ተዋጊዎች የጦር መሳሪያ የጫነ መርከብ ነው ብለው ተናግረው ነበር ። በኋላ ደግሞ የጦር መሳሪያ መጋዘን ላይ የታለመ ጥቃት ነው ማለታቸው ተጠቅሷል።

የሊቢያ የብሄራዊ ስምምነት መንግሥት በአጥቂዎቹ ላይ ዕርምጃ እስከሚወሰድ በሰላም ንግግሩ መሳተፍ እናቆማለን፤ እኛም በተገቢው ጊዜ የራሳችንን ዕርምጃ እንወስዳለን ብለዋል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG