ዋሺንግተን ዲሲ —
በተመድ የዩናይትድ ስቴትስ አምባሳደር ኒኪ ሄሊ ሥልጣናቸውን ለቀቁ። ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ በኋይት ሀውስ ከአምባሳደሯ ጋር ከተነጋገሩ በኋላ በሰጡት ቃል፣ አምባሳደር ሄሊ በዓመቱ መጨረሻ ላይ ሥልጣናችውን እንደሚለቁ ገልፀዋል።
ትራምፕ፣ አምባሳደር ሄሌ በሌላ ሥልጣን የአስተዳደሪ አካል እንደሚሆኑ ተስፋ አደርጋለሁ»።
ኒኪ ሄሊ በተመድ ዩናይትድ ስቴትስን ከመወከላቸው አስቀድሞ፣ የደቡብ ካሮላይና ገዢ በመሆን፣ ያን ቦታ በመያዝ የመጀመሪያዋ ሴት ባለሥልጣን ነበሩ።
እአአ በ2014 እንደገና መመረጣቸውም ይታወቃል።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ