በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ተመድ ለኢትዮጵያ አስቸኳይ የሰብዓዊ እርዳታ 40 ሚሊዮን ዶላር መደበ


ፎቶ ፋይል፦ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ ጉዳዮች ረዳት ዋና ጸሐፊ ማርቲን ግሪፊትስ
ፎቶ ፋይል፦ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ ጉዳዮች ረዳት ዋና ጸሐፊ ማርቲን ግሪፊትስ

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ ኮሚሽን ኃላፊ ማርቲን ግሪፊትስ፣ ከድርጅቱ ማዕከላዊ የአስቸኳይ ጊዜ ምላሽ ፈንድ፣ 25 ሚሊዮን ዶላር፣ በኢትዮጵያ ላለው የነፍስ አድንና፣ ሰብዓዊ እርዳታ ሥራዎች እንዲውል መመደባቸውን አስታውቀዋል፡፡

በኢትዮጵያ ውስጥ ካለው የኢትዮጵያ ሰብዓዊ ፈንድ ከተመደበው 15 ሚሊዮን ዶላር ጋር ተደምሮ፣ ለኢትዮጵያ ጠቅላላ ሰብዓዊ እርዳታ የተመደበው ወደ 40 ሚሊዮን ዶላር ማደጉን በዛሬው መግለጫቸው አመልክተዋል፡፡

በቅርቡ ኢትዮጵያን ጎብኝተው የተመለሱት ግሪፊትስ በሰሜን ኢትዮጵያ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች እያደገና እየተስፋፋ ባለው የሰብዓዊ ቀውስ ውስጥ እጅግ አደገኛ በሆነ ሁኔታ ላይ የሚገኙ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡

ከሁለቱም ክፍሎች የተገኘው ገንዘብ፣ በኢትዮጵያ የሚሰሩ የእርዳታ ድርጅቶች እጅግ አጣዳፊ የሆነ እርዳታ የሚያስፈልጋቸው በትግራይ፣ አማራና አፋር የሚገኙ ሰዎችን ለመታደግና ለመርዳት እንዲጠቀሙበት ይረዳቸዋል ብለዋል፡፡

XS
SM
MD
LG