በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ተመድ በሱዳን፣ ሔይቲ፣ ቡርኪናፋሶ እና ማሊ የረኀብ አደጋ ሊያጋጥም እንደሚችል አስጠነቀቀ


ተመድ በሱዳን፣ ሔይቲ፣ ቡርኪናፋሶ እና ማሊ የረኀብ አደጋ ሊያጋጥም እንደሚችል አስጠነቀቀ
please wait

No media source currently available

0:00 0:02:17 0:00

ተመድ በሱዳን፣ ሔይቲ፣ ቡርኪናፋሶ እና ማሊ የረኀብ አደጋ ሊያጋጥም እንደሚችል አስጠነቀቀ

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ተቋም የኾኑት የዓለም ምግብ ድርጅት እና የዓለም ምግብ እና እርሻ ድርጅት (FAO) በጋራ ባወጡት ሪፖርት፣ በዓለም ዙሪያ ከምግብ አቅርቦት ጋራ የተያያዙ አፋጣኝ ርዳታ የሚሹ አደጋዎች እየጨመሩ እንደኾነ አስታውቀዋል። በተለይም፣ በሱዳኑ ጦርነት እና ሔይቲ፣ ቡርኪናፋሶ፣ እና ማሊ፥ በሰዎች እና በሸቀጦች ላይ በጣሉት የእንቅስቃሴ ገደብ ምክንያት፣ የረኀብ አደጋ እየጨምረ መምጣቱን ተቋማቱ አመልክተዋል።

አራቱ ሀገራት፣ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ለረኀብ መጋለጣቸውን ወይም ማኅበረሰባቸው ወደ "አስከፊ ኹኔታ እየገቡ" መኾናቸውን ለይቶ፣ ቀደም ሲል በከፍተኛ ማስጠንቀቂያ ደረጃ ላይ ካስቀመጣቸው፥ አፍጋኒስታን፣ ናይጄሪያ፣ ሶማልያ፣ ደቡብ ሱዳንና የመን ጋራ ተቀላቅለዋል።

የመንግሥታቱ ድርጅት ተቋማት፣ በሪፖርታቸው፣ በከፍተኛ ደረጃ አሳሳቢ ኹኔታ ላይ ይገኛሉ፤ ካሏቸው ዘጠኝ ሀገራት በተጨማሪ፣ ሌሎች 22 ሀገራትም፣ ለከፍተኛ የምግብ ዋስትና ዕጦት በመጋለጣቸው፣ "አስጊ ኹኔታ ላይ ናቸው፤" ሲሉ፣ ለይተው አስቀምጠዋቸዋል። የሰዎችን ሕይወት እና እየጠፋ ያለውን የሥራ ዕድል ለማዳንም አስቸኳይ ትኩረት ሊሰጠው እንደሚገባ ጠይቀዋል።

"ዓለም አቀፍ የምግብ ዋስትናን ማረጋገጥ እና ማንም ወደ ኋላ እንደማይቀር ለማረጋገጥ ከፈለግን፣ አሁን የተደቀነብንን አደጋ፣ በተለመደው መንገድ ማስተናገድ ከአሁን ወዲያ አማራጭ አይኾንም፤" ብለዋል፣ የዓለም ምግብ እና እርሻ ድርጅት ዋና ጸሐፊ ኩ ዶንዡ። አያይዘውም፣ ሰዎችን ከረኀብ አፋፍ ለመመለስ፣ ሕይወታቸውን መልሰው እንዲገነቡ ለመርዳት እና ለምግብ ዋስትና ማጣት የሚዳርጉ መንሥኤዎችን በዘላቂነት ለመፍታት፣ በግብርናው ዘርፍ አፋጣኝ ርምጃ እንዲወሰድ ጠይቀዋል።

የመንግሥታቱ ድርጅት ሪፖርት፣ በሱዳን ያለው ግጭት ወደ ጎረቤት ሀገራትም ሊሻገር ይችላል፤ የሚለው ስጋት፣ በአካባቢው ድኻ ሀገራት ላይ፣ የኢኮኖሚ ቀውሱን ሊያባብስ እንደሚችል አስታውቋል። እ.አ.አ በ2023፣ ሊደርስ ይችላል ተብሎ ለሚጠበቀው ኤል-ኒኖ ለተሰኘው የአየር ንብረት መዛባት ተጋላጭ በኾኑ ሀገራት፣ የከፋ የአየር ንብረት ኹናቴዎችን ሊያስከትል ይችላል፤ የሚል ፍራቻም እንዳለ አመልክቷል።

XS
SM
MD
LG