በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ለሱዳናውያን የ4.1 ቢሊዮን ዶላር ዕርዳታ ተጠየቀ


ፎቶ ፋይል፦ ግጭቱን ሸሽተው የሚጓዙ ሱዳናውያን አድሬ፣ ቻድ እአአ 2/2023
ፎቶ ፋይል፦ ግጭቱን ሸሽተው የሚጓዙ ሱዳናውያን አድሬ፣ ቻድ እአአ 2/2023

በሱዳን ተቀናቃኝ ጀኔራሎች መካከል በሚካሄደውና አንድ ዓመት ሊሞላው በተቃረበው ጦርነት ምክንያት፣ በአገሪቱ የሚገኙ ሲቪሎች አንዳንዶቹ በረሃብ እየሞቱ ሳይሆኑ እንደማይቀር ምልክት በመታየት ላይ ነው በሚል፣ የተመድ የሰብዓዊ እና የፍልሰት ድርጅቶች የ4.1 ቢሊዮን ዶላር ርዳታ ጥሪ አቅርበዋል።

የተመድ የፍልሰተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን (UNHCR) እና የሰብዓዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ቢሮው (UNOCHA) በጋራ ባቀረቡት ጥሪ፣ ከሱዳን ሕዝብ ግማሽ የሚሆነው ወይም 25 ሚሊዮኑ ድጋፍና ከለላ ያስፈልጋቸዋል ብለዋል።

የተጠየቀው የገንዘብ ርዳታ በሱዳን ለሚገኙት፣ እንዲሁም ጦርነትን ሽሽት አገሪቱን ጥለው ለወጡትን ለመርዳት እንደሚውል ድርጅቶቹ አስታውቀዋል።

ደጋግመን ከእነርሱ የምንሰማው መልዕክት፣ ወደ ቤታቸው ተመልሰው ሕይወታቸውን መቀጠል እንደሚፈልጉ ነው”

ሱዳናውያኑ “ብዙ አጥተዋል” ያሉትና፣ ከሱዳን ተፈናቅለው በኢትዮጵያ ከሚገኙት ሱዳናውያን ጋር በቅርቡ የተነጋገሩት የተመድ የፍልሰተኞች ከፍተኛ ኮሚሽነር ፊሊፖ ግራንዲ፣ “ደጋግመን ከእነርሱ የምንሰማው መልዕክት፣ ወደ ቤታቸው ተመልሰው ሕይወታቸውን መቀጠል እንደሚፈልጉ ነው” ሲሉ አክለዋል።

ፈናቃዮቹ በአስቸኳይ ርዳታ እንደሚያሻቸውም ኮሚሽነሩ አስታውቀዋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG